ኮት ዲቯር በትራፊክ አደጋ መበራከት ምክንያት ሁሉንም መንጃ ፍቃድ አሰልጠኞች አገደች
የመንጃ ፈቃድ ፈተናን የሚሰጡ አሰልጣኞች ከሰልጣኖች ጉቦ ተቀብለው ፈተና እንዲያልፉ ያደርጋሉ በሚል ይከሰሳሉ
በኮት ዲቯር በየዓመቱ በአማይ 1 ሺህ 400 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያጣሉ
የኮት ዲቯር መንግስት በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉንም የመንጃ ፈቃድ አሰልጣኖችን “በዘርፉ ያለውን ብልሹ አሰራር ለማጽዳት” በሚል ማገዱ ተሰምቷል።
ሀገሪቱ ውሳኔውን ያሳለፈችው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ እየተበራከተ ባለው የትራፊክ አደጋ ሳቢያ ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጠቱን ተከትሎ መሆኑን የሲ.ጂ.ቲኤ.ን ዘገባ ያመላክታል።
የኮት ዲቯር የትራንስፖርት ሚኒስትር አማዱ ኮኔ እንደተናገሩት፤ “ሀገሪቱ ፖሊስ ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ለ3 ወራት የመንጃ ፈቃድ ፈተና አሰጣጡን የሚከታተል ይሆናል” ብለዋል።
“ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ የትራፊክ አደጋዎች በተበላሹ መንገዶች ሳይሆን፤ በሰዎች በሚሰራ ስህተት ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፤ ከመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚሰሩ ወንጀሎችን ጨምሮ በርክታ ምክንያቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።
በኮት ዲቯር በየዓመቱ በአማይ 1 ሺህ 400 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን የሚያጡ ሲሆን፤ በያዝነው ወር ብቻ 140 ሰዎች በትራፊፊክ አደጋ ህይወታቸው አልፏል።
በሀገሪቱ የመንጃ ፈቃድ ፈተናን የሚሰጡ አሰልጣኞች የመንጃ ፈቃድ ሰልጣኖች የአሽከርካሪነት ፈተናን በቀላሉ እንዲያልፉ ጉቦ ይቀበላሉ በሚል ይከሰሳሉ።