በፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ በሀገሪቱ መከሰት የጀመረው የጅሃድ ጥቃት አሁን ወደ መሃል ሀገርና ጎረቤት ቡርኪናፋሶና ኒጀር ተስፋፍቷል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ቃል አቀባይ እንዳስታወቀው ቁጥራቸው 20 የሚሆኑ የተመድ ሰላም አስከባሪዎች በማሊ በሚገኘው ካምፓቸው ጥቃት ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡
በጦርነት በተበታተነችው ከረና መንደር በሚገኘው ጊዜያዊ ካምፕ ነበር ጥቃቱ የደረሰው፡፡ ኦሊቨር ሳልጋዶ የተባለው ለተመድ 13ሺ አባላት ላሉት ሚኒሱማ ተልእኮ ቃል አቀባይ ቦታው በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተኩሳ መጠቃቱን ገልጿል፡፡
ማሊ ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ በሀገሪቱ የጅሃድ ጥቃት ከተከፈተባት በኋላ ጥቀቱ ወደ መሃል የሀገርና ወደ ጎረቤት ቡርኪናፋሶና ኒጀር ተስፋፍቷል፡፡
በሺዎች የሚቆጠሩ ወደታሮችና ንጹሃን ተገድለዋል፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ቤታቸውን ለቀው ተፈናቅለዋል፡፡ ማእከላዊ ማሊ የግጭቱ ማእከል ከሆነ በኋላ በወታደሮችና በጎሳ መነሻ ያደረገ ግድያ የተለመደ ሆኗል፡፡