ስልጣንን የተቆጣጠሩት ወታደሮች ጫና ሲበረታባቸው ስልጣን የ18 ወራት እድሜ ላለው ጊዜያዊ ሲቪል መንግስት ሰጥተዋል
የማሊ ጊዜያዊ ህግ አውጭ አካል በማሊ በነሃሴ ወር በተካሄደው መፈንቅለ መንግስት ቁልፍ ሚና የነበረውን ኮሎኔል ማሊክ ዲያውን ኃላፊ አድርጎ ሾሟል፡፡ ወታደሩ በፖለቲካ ያለው ተሳትፎ በሀገሪቱ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡
121 አባላት ያሉት የሀገሪቱ የሽግግር ምክርቤት ስብሰባውን በማሊ ዋና ከተማ ባማኮ ጀምሯል፡፡ ስብሰባው በሳህል ቀጣና የምትገኘው ሀገር ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንድትመለስ የጎላ ሚኛ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የማሊ መንግስት የጂሃዲስትን እንቅስቃሴና በሀገሪቱ አለ የሚባለውን ሙስና በመከላከል አለመቻሉን ተከትሎ ከመጣው ተቃውሞ ሳምንታት በኋላ ወጣት ወታደሮች ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ቦበካር ኬይታን ከስልጣን አውርደዋቸዋል፡፡
ስልጣንን የተቆጣጠሩት ወታደሮች አለምአቀፍ ጫና ሲበረታባቸው ስልጣናቸውን የ18 ወራት እድሜ ላለው ጊዜያዊ መንግስት አስረክበዋል፡፡ ነገርግን ከወታደሩ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች በጊዜያዊ መንግስት መካተታቸው ቁጣን አስነስቷል፡፡
የመፈንቅለ መንግስት መሪው አሲሚ ጎይታ ጊዜያዊ ምክትል ፕሬዘዳንት ሆነው ሲመረጡ፣ ጡረታ ወጥተው የነበሩት ባህ ንዳው ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ተችዎች ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት ለመምረጥ ረጅም ጊዜ ወስዷል ብለዋል፡፡
በሽግግር ምክርቤቱ የንግድ ማህበረሰብና የሲቪል ሶሳይቲ መወመጫ ያላቸው ሲሆን የመከላከያና የጸጥታ ከጠቅላላ መቀመጫዎች ሀይሎች 22ቱን ይወሳዷሉ፡፡