በነሀሴ ወር በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተነሱት ኬይታ ምንም ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም፤ ቀጣይ እርምጃቸውንም አላሳወቁም
በነሀሴ ወር በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተነሱት ኬይታ ምንም ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም፤ ቀጣይ እርምጃቸውንም አላሳወቁም
በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተወገዱት የማሊው ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ቦባካር ኬይታ በትናንትናው እለት ለስድስት ሳምንታት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሲታከሙ ከቆዩ በኋላ ወደ ሀገራቸው ማሊ ተመልሰዋል፡፡
በነሀሴ ወር በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተነሱት ኬይታ ምንም ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም፤ ቀጣይ እርምጃቸውንም አላሳወቁም፡፡ የ75አመቱ መሪ ከስልጣን የተወገዱት መንግስታቸው ከእስላሚዊና የጉሳ ታጣዎች አልታደገንም በማለት ተቃውሞ ከተነሳባቸው በኋላ ነው፡፡
መፈንቅለ መንግስቱ ከተካሄደ ከስድስት ቀን በኋላ በህዝብ ይፋ ባልሆነ ምክንያት ወደ አቡዳቢ መብረር ችለዋል፡፡
የምእራብ አፍሪካ ሀገራት በመጀመሪያ ኬይታ ወደ ስልጣን እንዲመለሱ ይፈልጉ ነበር፤ ነገርግን ለዚህ ፍላጎት ዝቅተኛ ፍለጎት መኖሩን ከተረዱ በኋላ ጥያቄውን ትትታል፡፡
ምንም እንኳን ኬይታ ከሄዱ በኋላ መፈንቅለ መንግስቱን የመራው ቡድን ስልጣንን ለይስሙላ ሲቪል ቢያስረክብም ፕሬዘዳንት የሆኑት ጡረታ የወጡ ኮሎኔል ሲሆኑ ምክትሉ ደግሞ የመፈንቅለ መንግስት መሪ የነሩት ናቸው፡፡
የኬይታ ተቃዋሚዎች ኬይታ በፕሬዘዳንታዊ አውሮፕላን ግዠና በወታደራዊ እቃ ግዥ ሙስና ሰርተዋል ይከሰሱ ይላሉ፤ ነገርግን ኬይታ ክሱን አይቀበሉትም፡፡