የንዳውን ቃል መሃላ ተከትሎ የምእራብ አፍሪካ ሀገራት በማሊ ላይ የጣሉትን ማእቀብ ያነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል
የንዳውን ቃል መሃላ ተከትሎ የምእራብ አፍሪካ ሀገራት በማሊ ላይ የጣሉትን ማእቀብ ያነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል
ጡረታ የወጡት የማሊ ኮሎኔል ንዳው በማሊ በፈረንጆቹ ነሀሴ 18 የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ወደ ሰላማዊ መንግስት እንዲሸጋገር ሀገሪቱን ለ18 ወራት እንዲመሩ ቃለ መሃላ ፈጸሙ፡፡
መፈንቅለ መንግስቱን የመሩት ኮሎኔል አሲማ ጎይታ የሽግግር መንግስቱ ምክትል እንዲሆኑ ባማኮ በተካሄደው ስነስርአት ተመርጠዋል፡፡
የማሊ ባለስልጣናት የምእራብ አፍሪካ ሀገራት ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ቦባከር ኬይታ በመፈንቅለ መንግስት ከተወገዱ በኋላ በማሊ ላይ የጣሉት የኢኮኖሚ ማእቀብ ይነሳል ብለው ተስፋ አድርገዋል፡፡
ባለፈው ወር በመፈንቅለ መንግስት የሀሪቱን ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ቦበከር ኬይታን ከስልጣን ያወረደው ቡድን ስልጣኑን ለሰላማዊ ሰዎች እንዲያስተላለፍ የጎረቤት ሀገራት ጠንካራ ግፊት ሲያሳድሩ ቆይተዋል፡፡
15 አባል ሀገራት ያሉት የምእራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ድርጅት መልእክተኛ ጉድለክ ጆናታን ማእቀቡ ንዳው ቃለመሃላ ከፈጸሙ በኋላ ይነሳል ብለዋል፡፡