በመጠናቀቅ ላይ ያለው 2023 ዓመት ላለፉት ስድስት ተከታታይ ወራት በታሪክ ከፍተኛ ሙቀት ተመዝግቦባቸዋል
የያዝነው 2023 ዓመት በታሪክ ሞቃታማው ዓመት እንደሚሆን ተገለጸ፡፡
የአውሮፓ ኮፐርኒከስ ኦበሰርቫቶሪ ባወጣው ሪፖርት የተያዘው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት በታሪክ ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበበት ዓመት ሆኖ ሊጠናቀቅ እንደሚችል አስታውቋል፤፡
የኦብዘርቫቶሪው ምክትል ምክትል ሀላፊ ሳማንታ በርግስ እንዳሉት ያሳለፍነው ሕዳር ወር ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበበት ወር ሆኖ አልፏል ብለዋል፡፡
በሕዳር ወር የተመዘገበው ሙቀት በዚሁ ዓመት ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገባበቸው ወር በሚል ተለይተው የነ በረውን ሪከርድ ሰብሯልም ተብሏል፡፡
ያሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ምድራችን በታሪክ ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበበት ወር ተብሎ የተያዘ ቢሆንም ይህ የሙቀጥ መጠን በየወሩ እየጨመረ መጥቷል፡፡
ያሳለፍነው ህዳር ወርም ከ100 ዓመት በፊት በኢንዱስትሪ ዘመን ከነበረው ሙቀት የበለጠ ሙቀት ተመዝግቦበት አልፏልም ተብሏል፡፡
የፈረንጆቹ 2023 ዓመት የመጨረሻ ወር የሆነው ታህሳስ ከገባ ስድስተኛ ቀኑ ላይ ሲሆን ይህም በህዳር ወር ከተመዘገበው ሙቀት የበለጠ ሙት ሊመዘገብበት እንደሚችልም ኦብሰርቫቶሪው አስታውቋል፡፡
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ሰባተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የዓለም ቢዝነስ ተቋማት ለአየር ንብረት ለውጥ ድጋፍ 5 ቢሊዮን ዶላር አዋጡ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር በመምከር ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ ከ200 በላይ ሀገራት መሪዎች እና ባለሙያዎች መካከል 117 ሀገራት በ2030 የታዳሽ ሀይል አቅርቦቶቻቸውን እንደሚያሻሽሉ ተናግረዋል፡፡
70 መንፈግስታት እና 39 ተቋማትም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በጋራ ለመስራት ስምምነቶችን የተፈራረሙ ሲሆን ለአደጋ ተጋላጭ ሀገራትን እንደሚደግፉም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡