መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአየር ንብረት ፖሊሲ ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ
ማህበረብ ስለአየር ንብረት ለውጥ ግንዛቤ እንዲኖረው ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ
ድርጅቶች ፖሊሲ አውጭዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩት በጥናት ላይ የተመሰረተ መረጃ በማቅረብ ነው
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአየር ንብረት ፖሊሲ ላይ ተጽእኖ አላቸው።
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በጥናት፣ በአድቮኬሲ እና በማስተባበር ስራ በአየር ንብረት ፖሊሲዎች ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ።
እነዚህ ድርጅቶች በማግባባት እና ግንዛቤ በማስጨበጥ በአለምአቀፍ ደረጃ የፖሊሲ ለውጦች እንዲኖሩ የራሳቸው ሚና አላቸው።
ድርጅቶች ፖሊሲ አውጭዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩት በጥናት ላይ የተመሰረተ መረጃ በማቅረብ ነው።
መረጃ ከማቅረብ በተጨማሪ ድርጅቶች ከፖሊሲ አውጭዎች፣ ከንግድ ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካት ጋር በትብብር በመስራት የፖሊሲ ለውጥ እንዲኖር ጥረት ያደርጋሉ።
ማህበረብ ስለአየር ንብረት ለውጥ ግንዛቤ እንዲኖረው ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።
በአለምአቀፍ ደረጃ ያለውን የሙቀት መጠን ከ2 ዲግሪ ሴልሺየስ እንዳይበልጥ ተመድ እና አለምአቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጥረት እያደረጉ ናቸው።
በአረብ ኢምሬትስ እየተካሄደ ባለው የከፕ28 ስብሰባ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎቸን እና ሀገራትን የሚውል ፈንድ እንዲንቀሳቀስ ተስማምተዋል።