በዓለም ቀዳሚ የጎብኝዎች መዳረሻ የሆኑ ከተሞች የትኞቹ ናቸው?
'ዩሮሞኒተር ኢንተርናሽናል' የተባለው አለምቀፍ የገቢያ አጥኚ ኩባንያ በ2033 በዓለም ቀዳሚ የጎብኝዎች መዳረሻ የሆኑትን 10 ከተሞች በደረጃ አስቀምጧል
ኩባንያው ባወጣው ሪፖርት መሰረት የቱርኳ ኢስታንቡል ቀዳሚ የዓለም ማራኪ የጎብኝዎች መዳረሻ ሆናለች
በ2023 ከዓለም ቀዳሚ የጎብኝዎች መዳረሻ የሆኑ ከተሞች የትኞቹ ናቸው?
'ዩሮሞኒተር ኢንተርናሽናል' የተባለው አለምቀፍ የገቢያ አጥኚ ኩባንያ በ2033 በዓለም ቀዳሚ የጎብኝዎች መዳረሻ የሆኑትን 10 ከተሞች በደረጃ አስቀምጧል።
ኩባንያው ባወጣው ሪፖርት መሰረት የቱርኳ ኢስታንቡል ቀዳሚ የዓለም ማራኪ የጎብኝዎች መዳረሻ ሆናለች።
ኢስታንቡል ከዚህ በፊት ጉብኝት ሲባል ወደ አእምሮአችን የሚጡትን ፓሪስን፣ ለንደንን ወይም ባንኮክን በልጣ ቀዳሚ መዳረሻ መሆኗ ግርምትን ፈጥሯል።
ከኢስታንበል በተጨማሪ ሌላኛዋ የቱርክ ከተማ አንታሊያ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
በ2023፣ 202.2 ሚሊዮን ሰዎች ቱርክን መጎብኘታቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል።
ዩሮሞኒተር ባለፈው ታህሳስ ወር ባወጣው ሪፖርት እንደጠቀሰው ኢስታንቡልን የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር በየአመቱ በ26 በመቶ ሲያድግ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን ለንደን እና ዱባይን የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ በተከታታይ በ17 እና በ18 በመቶ አድጓል።
ኢስታንቡል በአውሮፖ 15 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት ትልቅ ከተማ በመሆኗ ቀዳሚ መሆኗ ላያስገርም ይችል ይሆናል። ነገርግን ሊያስገርም የሚችለው 1.3 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት አንታሊያ እንዴት ከፓሪስ እና ሆንግኮንግ በልጣ በ16.5 ሚሊዮን አለምቀፍ ጎብኝዎች ተጎበኘች የሚለው ነው።
አንታሊያ አረንጓዴ የሚመስል ውሃዋ፣ ቀላል ክረምቷ እና ለ300 ቀናት ጸሀይ የማይለያት መሆኗ በጎብኝዎች ተመራጭ እንድትሆን አድርጓታል ተብሏል።
በዩሮሞኒተር ኢንተርናሽናል መረጃ መሰረት በ2023፣ ከዓለም ቀዳሚ የጎብኝዎች መዳረሻ የሆኑት 10 ከተሞች የሚከተሉት ናቸው።
1 ኢስታንቡል
2 ለንደን
3 ዱባይ
4 አንታሊያ
5 ፓሪስ
6 ሆንግ ኮንግ
7 ባንኮክ
8 ኒው ዮርክ
9 ካንክን
10 መካ