ቱርክ በኢስታንቡል ፍንዳታ የጠረጠረችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዋለች
በኢስታንቡል ትናንት እሁድ በደረሰው ፍንዳታ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ 81 ሰዎች ቆስለዋል
ቱርክ ለፍንዳታው የኩርድ ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርጋለች
ቱርክ ለኢስታንቡል ፍንዳታ ቦምብ ጣለው ያለችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሱሌይማን ሶይሉ ተናግረዋል።
ሮይተርስ የቱርክ የዜና ወኪልን አናዶሉ ጠቅሶ እንደዘገበው ፖሊስ በፍንዳታ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል።
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲጵ ጣይብ ኤርዶጋን "ሽብርተኝነትን የሚሸት" ባሉት የቦምብ ጥቃት በኢስታንቡል ከተማ በሚገኘው ኢስቲካል ጎዳና በተጨናነቀ የእግረኞች ጎዳና ላይ የደረሰ ነው። በፍንዳታ እስካሁን የስድስት ሰዎች ህይዌ ሲያልፍ፤ 81 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ነው የተባለው።
ቱርክ ለፍንዳታው የኩርድ ታጣቂዎችን መውቀሷን ሮይተርስ ዘግቧል።
በተጨናነቀና ታሪካዊ በተባለው የኢስታንቡል የገበያ ጎዳና ላይ ለደረሰው ፍንዳታ፤ ቦንምቡን በመትከል የተጠረጠረችውን ሶሪያዊት ሴት ጨምሮ ፖሊስ 47 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
የኢስታንቡል ፖሊስ ተጠርጣሪዋን ሶሪያዊ አህላም አልባሺር ሲል ሰይሟል።
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሱሌይማን ሶይሉ እሁድ እለት በኢስቲካል ጎዳና ላይ ለደረሰው ፍንዳታ የኩርዲስታን ሰራተኞች ፓርቲ (ፒኬኬ) እና የሶሪያ ኩርዲሽ ታጣቂዎች ተጠያቂ ናቸው ብለዋል።
እንደ ኢስታንቡሉ ንዳታ አይነት ተመሳሳይ ክስተቶች ባለፉት ዓመታት መፈጸማቸውን ዘገባው አስታውሷል።