ከዱባይ እስከ ሙምባይ፤ ከእሲስታንቡል እስከ ቤጂንግ ሚሊየኖች በአደባባይ አሮጌውን አመት ሸኝተው አዲሱን ተቀብለዋል
የጎርጎሮሳውያንን የዘመን ቀመር የሚከተሉ ሀገራት የ2024 አዲስ አመትን በመቀበል ላይ ናቸው።
በመላው አለም 39 የተለያየ የስአት አቆጣጠር ያላቸው ሀገራት አዲሱን አመት የሚያከብሩ እንደመሆናቸው 2024ን ለመቀበል 26 ስአታት ይወስዳል።
የገና ደሴት እየተባለች የምትጠራው የፓስፊኳ ኪሪባቲ አዲሱን አመት በማክበር ቀዳሚዋ ሆና ቀጥላለች፤ ጎረቤቶቿ ሳሙኣ እና ቶንጋም ተከትለዋት አክብረዋል።
የአሜሪካዋ ሃዋይ አዲሱን አመት ዘግይተው ከሚቀበሉት መካከል ተጠቃሽ ናት።
የለንደን፣ ዱባይ፤ አንካራ እና ሌጎስ ሰማይ የ2024 አመት መግባትን በሚያበስሩ ርችቶች ደምቀው አምሽተዋል።
በ2024 አቀባበል ወቅት የበርካቶችን ቀልብ ከያዙ ምስሎች የተወሰኑትን እነሆ፦
በርችቶች የደመቀው የአዲስ አመት አቀባበል በሪዮ ደኔጄሮ ኮፓካባና የባህር ዳርቻ - ብራዚል
የጀርመኗ ሙኒክ ሌሊቱን የአዲሱን አመት መግባት በሚያበስሩ ርችቶች ፈክታለች
በእንግሊዝ የዌስትሚኒስተር ስአት በርችቶች ደምቆ የ2024 መግባትን አብስሯል
የፈረንሳይ መዲና ፓሪስ አዲሱን አመት ስትቀበል
የበዓል አብሳሪ ርችቶች በታሪካዊቷ አቴንስ
በቱርክ መዲና አንካራ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አዲሱን አመት በደስታ ሲቀበሉ
በርካቶች በጉጉት የጠበቁት የአዲስ አመት አቀባበል በሰርቢያዋ ቤልግሬድ
ጎረቤቷ ጦርነት ታውጅብኛለችበሚል ስጋት ውስጥ የምትገኘው ደቡብ ኮሪያ ሰማይ ላይ የዘንዶ ምስል በሰሩ ድሮኖች አዲሱን አመት ተቀብላለች
በናይጀሪያ መዲና ሌጎስ የ2024 መቀበያ የሙዚቃ ኮንሰርት
የኮሮና ወረርሽኝ መነሻ ናት በሚል ስትወቀስ የቆየችው የቻይናዋ ውሃን ከተማም ወደ ሰማይ ፊኛዎችን በመልቀቅ በልዩ ድባብ አዲሱን አመት ተቀብላለች
የዱባዩ የአለማችን ረጅም ህንጻ ቡርጀ ከሊፋም እንደተለመደው በርችቶች ደምቆ አምሽቷል