የአውሮፓ ጠንቋዮች እና የ2024 ግምቶቻቸው ምን ምን ናቸው?
የፈረንሳዩ ኖስትራዳሙስ ቡልጋሪያዊቷ ባባ ቫንጋ የተሰኙት ጠንቋዮች የ2024 አበይት ክስተቶችን ተናግረዋል

የፕሬዝዳንት ፑቲን ግድያ፣ አዲስ ቴክኖሎጂ ይፈበረካል፣ ከባድ የአየር ንብረት ለውጥ የከሰታል፣ ዓለማችን አዲስ ጦርነት ታስተናግዳለች እና እንደ ካንሰር ላሉ ገዳይ ሕመሞች ደግሞ መድሃኒት ይገኛል ሲሉ
የአውሮፓ ጠንቋዮች እና የ2024 ግምቶቻቸው ምን ምን ናቸው?
አውሮፓዊያኑ የፈረንሳዩ ኖስትራዳሙስ እና ቡልጋሪያዊቷ ባባ ቫንጋ የተሰኙት ጠንቋዮች በየዓመቱ ሊከሰቱ የሚችሉ አበይት ክስተቶችን በመጠንቆል ይታወቃሉ፡፡
እነዚህ ሁለት አውሮፓዊያን ጠንቋዮች ሊከሰቱ ይችላ ብለው ከተናገሯቸው ጥንቆላዎች ውስጥ የተወሰኑት መከሰታቸውን ተከትሎ በየዓመቱ እነዚህ ሰዎች ምን ይላሉ የሚለውን መስማት የብዙዎችን ትኩረት ይስባል፡፡
ቡልጋሪያዊቷ ባባ ከዚህ በፊት ተናግራቸው ከተፈጸሙ ክስተቶች መካከል ንግስት ዲያና ትሞታለች፣በአሜሪካ እና አውሮፓ ላይ የሽብር ጥቃት ይፈጻማል፣ ሶቪየት ህብረት ትፈራርሳለች፣ የሩሲያ መርከብ ትሰጥማለች እና ሌሎችንም ዋነኞቹ ናቸው ሲል ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የብሪታንያ ዩንቨርስቲ በአስማት እና ጥንቆላ የማስተርስ ድግሪ ማስተማር ሊጀምር ነው
የፈረንሳዩ ኖስትራዳሙስ ደግሞ አዶልፍ ሂትለር የሚባል መሪ እንደሚመጣ፣ ኮሮና ቫይረስ እንደሚከሰት ፣ ከባድ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚከሰት ተናገሯቸው የተፈጸሙ ክስተቶች ናቸው፡፡
እነዚህ የአውሮፓ ጠንቋዮች አዲሱ የፈረንጆች 2024 ዓመት ሊገባ ትንሽ ቀናት የቀረው ሲሆን በዚህ ዓመት ሊከሰቱ ይችላሉ ያሏቸው ዋና ዋና የዓለማችን ክስተቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
በዩክሬን ምድር ከምዕራባዊያን ጋር እየተዋጋን ነው የሚሉት የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይገደላሉ የሚለው አንዱ ሲሆን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ይሞታሉ፣ የዓለም ኢኮኖሚ ቀውስ ይከሰታል፣ ዓለማችን አዲስ ጦርነት ታስተናግዳለች የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ካንሰር እና የመርሳት ወይም አልዛይመር ሕመም ፈዋሽ መድሃኒት ይገኝላቸዋል፣ በብሪታንያ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ላይ ችግር ይፈጠራል በዚህም ልዑል ሀሪ ንጉስ ይሆናሉ፣ ድርቅ እና ጎርፍ ይከሰታል የሚሉት ከትንቢቶቹ መካከል ተጠቅሰዋል፡፡
እንዲሁም በአውሮፓ የሽብር ጥቃቶች ይስፋፋሉ የተባለ ሲሆን በቤተ ሙከራ የለማ ቫይረስ ምክንያት ለዓለም ከባድ የሆነ የጤና ችግር ይከሰታል፣ አዲስ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፈጠራ ከመገኘቱ በላይ ዓለማችን በሳይበር ጥቃት ትታመሳለችም ሲሉ ጠንቋዮቹ ተንብየዋል፡፡
እነዚህ አውሮፓዊን ጠንቋዮች በህይወት የሌሉ ሲሆን ህይወታቸው ከማለፉ በፊት እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በየዓመቱ ሊከሰቱ የሚችሉ ክስተቶችን ጽፈዋል፡፡