በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ዋዜማ በአውሮፓ በተተኮሱ ርችቶች የሰዎች ህይወት አለፈ
ለበዓል ዋዜማ በተተኮሱ ርችቶች በጀርመን፣ በኔዘርላንድስ እነ ኦስትሪያ ሰው ህይወት አልፏል
በኔዘርላንድስ ብቻ ለበዓል ማድመቂያ በተተኮሱ ርችቶች ከ80 በላይ ሰዎች ቆስለዋል
በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራ ለ2022 አዲስ ዓመት ዋዜማ በተተኮሱ ርችቶች በሰዎች ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ።
ለበዓል ዋዜማ በተተኮሱ ርችቶቹ በጀርመን እና በኔዘርላንድ የ3 ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ ምክንያት መሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በኔዘርላንድስ አንድ ግለሰብ በቤቱ ውስጥ የሰራውን ርችት ሲቶክስ በመመልከት ላይ የነበረ የ12 ዓመት ታዳጊ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፤ ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ከፍኛ መጎዳቱ ተነግሯል።
በተጨማሪም በኔዘርላንድ ከ80 በላይ ሰዎች ላይ በርችቶች አማካኝነት ጉዳት ደርሷል የተባለ ሲሆን፤ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል እጅና እግራቸውን ያጡ እንዳሉ ታውቋል።
በጀርመን ሄኔፍ ከተማ በተተኮሰ ርችትምን አንድ የ37 ዓመት ጎልማሳ ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።
በሌሎች የጀርመን ከተሞችም ለበዓል ማድመቂያ በበተኮሱ ርችቶች በርካቶች ላይ የተለያየ ነጠን ጉዳት መድረሱን ያስታወቀው ፖሊስ፤ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል።
በተመሳሳይ በኦስትሪያም ለአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ማድመቂያ በተተኮሰው ርችት አንድ የ23 ዓመት ወጣት ህይወት ማለፉንም ነው የተገለፀው።