ሚሊየኖች አደባባይ በመውጣት 2024ን ሽኝተው አዲሱን አመት ተቀብለዋል
የጎርጎሮሳውያንን የዘመን ቀመር የሚከተሉ ሀገራት የ2025 አዲስ አመትን በመቀበል ላይ ናቸው።
በመላው አለም 39 የተለያየ የስአት አቆጣጠር ያላቸው ሀገራት አዲሱን አመት የሚያከብሩ እንደመሆናቸው 2025ን ለመቀበል 26 ስአታት ይወስዳል።
የገና ደሴት እየተባለች የምትጠራው የፓስፊኳ ኪሪባቲ አዲሱን አመት በማክበር ቀዳሚዋ ናት፤ ጎረቤቶቿ ሳሙኣ እና ቶንጋም ተከትለዋት አክብረዋል።
የአሜሪካዋ ሃዋይ አዲሱን አመት ዘግይተው ከሚቀበሉት መካከል ተጠቃሽ ናት።
የለንደን፣ ዱባይ፤ አንካራ እና ሌጎስ ሰማይ የ2025 አመት መግባትን በሚያበስሩ ርችቶች ደምቀው አምሽተዋል።
የአዲስ አመት አቀባበልን ከሚያሳዩ አስደናቂ ምስሎች የተወሰኑትን እነሆ፦
በኒውዮርክ ታይም ስኩዌር የአዲስ አመት አቀባበል
በርችቶች የደመቀው የአዲስ አመት አቀባበል በሪዮ ደኔጄሮ ኮፓካባና የባህር ዳርቻ - ብራዚል
በእንግሊዝ የዌስትሚኒስተር ስአት በርችቶች ደምቆ የ2025 መግባትን አብስሯል
ርችቶች በግብጽ ጊዛ ፒራሚዶችን ሲያደምቁ
ሶሪያውያን የበሽር አል አሳድ የ24 አመታት አገዛዝ ከተወገደ በኋላ አዲሱን አመት ሲቀበሉ
የአለማችን ረጅሙ ህንጻ ቡርጀ ከሊፋ በርችቶች የደመቀበት የ2025 አቀባበል - ዱባይ - አረብ ኤምሬትስ
በኢንዶኔሽያ ጃካርታ አንኮል በተሰኘው የባህር ዳርቻ ውብ የአዲስ አመት አቀባበል
የኮሮና ወረርሽኝ መነሻ ናት በሚል ስትወቀስ የቆየችው የቻይናዋ ውሃን ከተማም ወደ ሰማይ ፊኛዎችን በመልቀቅ በልዩ ድባብ አዲሱን አመት ተቀብላለች
በቶኪዮ የመንግስት መስሪያ ቤት ህንጻ የአዲሱን አመት መግባት ሲያበስር