ኢለን መስክ በኤክስ ገጹ ላይ ስሙን "ኬኪዩስ ማክሲመስ" በሚል መቀየሩ አነጋገረ
ታዋቂው ቢሊየነር መስክ የአሜሪካ ምርጫ 2024ን ላሸነፉት ትራምፕ ድጋፍ ካደረጉት ባለሀብቶች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው
ታዋቂው ቢሊየነር መስክ የአሜሪካ ምርጫ 2024ን ላሸነፉት ትራምፕ ድጋፍ ካደረጉት ባለሀብቶች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው
ኢለን መስክ በኤክስ ገጹ ላይ ስሙን "ኬኪዩስ ማክሲመስ" በሚል መቀየሩ አነጋገረ።
የአለም ቁጥር አንዱ ሀብታም ኢለን መስክ የራሱ በሆነው ማህበራዊ ሚዲያ ኤክስ ላይ ስሙን "ኬኪዩስ ማክሲመስ" በሚል ከቀረ በኋላ መነጋገር ሆኗል።
የቴክኖሎጂ ከበርቴው እና የተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሚስጥረኛ ስሙን የቀየረበትን እና በቀኝ ዘመም ቡድኖች የሚዘወተረውን አስቂኝ ምስል ወይም 'ሜም' ለምን 'ፕሮፋይል' እንዳደረገው እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።
ይህን ተከትሎ ተመሳሳይ ስም የሚጋራ ሜምኮይን ወይም ዲጂታል ከረንሲ እንዲነቃቃ በማድረግ የክሪፕቶከረንሲ ገበያ ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩን ቢቢሲ ዘግቧል።
ከዚህ ቀደም መስክ በማህበራዊ ሚዲያ በሰጠው አስተያየት በክሪፕቶ ገበያ ላይ ተጽዕኖ አሳድሮ የነበረ ቢሆንም በዚህ ሜምኮይን ላይ ተሳትፎ ስለማድረጉ ግልጽ አይደለም።
"ኬኪዩስ" የሚለው ቃል "ኬክ" ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ሲሆን በግርድፉ ሲተረጎም "ጮክ ብሎ መሳቅ" የሚል ነው። ቃሉ ታዋቂ የሆነው 'በጌመርስ' ወይም በተጨዋቾች ቢሆንም አሁን ግን ከቀኝ ዘመሞች ጋር ተያይዞ ነው ሁል ጊዜ የሚነሳው።
"ማክሲመስ" የሚለውን ብዙ ሰዎች በግላዲያተር ፊልም ላይ የጀግና ገጸ ባህሪ ወክሎ ከሰራው ሩዜል ክሮው ስም ጋር አመሳስለውታል።
ታዋቂው ቢሊየነር መስክ የአሜሪካ ምርጫ 2024ን ላሸነፉት ትራምፕ ድጋፍ ካደረጉት ባለሀብቶች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። መስክ ትራምፕ ምርጫ ካሸነፉ በኋላ በተለያዩ መድረኮች አብሯቸው ታይታል።
ትራምፕ የመንግስት አሰራርን ያቀላጥፋል ብለው ባቋቋሙት አዲስ ቢሮም ለመስክ ሹመት ሰጥተውታል።