የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን ከ124 ብር ጀምሮ እየገዙ እስከ 127 ብር እየሸጡ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ መጠነኛ ጭማሪ አድርጓል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.0086 ብር እየገዛ በ126.4888 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7128 ብር እየገዛ በ127.2071 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ገልጿል።
ዳሽን ባንክ ከአንድ ወር በፊት በፊት ያወጣውን ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር በመግዛት በ127.2114 ብር እየሸጠ ይገኛል።
አቢሲኒያ ባንክ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ124.7045 ብር እየሸጠ በ127.1986 ብር እየሸጠ ነው።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8086 ብር ገዝቶ በ127.3048 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ የታህሳስ 23 2017 የውጭ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7099 ብር ገዝቶ በ127.2041 ብር እየሸጠ መሆኑን ጠቁሟል።