በዘንድሮው የመውጫ ፈተና 22 የግል ትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸው ተገለጸ
ሚኒስትሩ እንደገለጹት ከሆነ 87 መቶ የሚሆኑት የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የተሰጣቸውን የመውጫ ፈተና አላለፉም
የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች ፈተናውን ማለፉ እስከሚችሉበት ጊዜ ድረስ ያለገደብ መፈተን ይችላሉ
በዘንድሮው የመውጫ ፈተና 22 የግል ትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸው ተገለጸ።
ትምህርት ሚኒስቴር ዘንድሮ በሰጠው የመውጫ ፈተና 22 ከፍተኛ የግል ትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።
ዶክተር ብርሃኑ ይህን ያሉት የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን በፈቃድ አሰጣጥ ስርአት ዙሪያ ባዘጋጀው ውውይት ላይ መሆኑን ባለስልጣኑ በፌስቡክ ገጹ ገልጿል።
ሚኒስትሩ እንደገለጹት ከሆነ 87 መቶ የሚሆኑት የግል የከፍተኛ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተሰጣቸውን የመውጫ ፈተና አላለፉም።
ፈተና ካስፈኑት የግል ትምህርት ተቋማት ውስጥ 22 ተቋማት አንድም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል ሚኒስተሩ።
ሚኒስትሩ በ2016 ዓ.ም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ውስጥ ማሳለፍ የቻሉት 13 በመቶ ሲሆን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ 58 በመቶ ማሳለፍ ችለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው የትምህርት ስርአት ማሳሻያ ፖሊሲ መሰረት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና(ኤግዚት ኤግዛም) መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች ፈተናውን ማለፉ እስከሚችሉበት ጊዜ ድረስ ያለገደብ መፈተን ይችላሉ።