የሩሲያው ዋግነር ተዋጊ ቡድን በማሊ በነበረው ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት አስታወቀ
ማሊ ግን በግዛቷ ያሉት የዋግነር ቅጥረኞች ሳይሆኑ ለወታሮቿ የሩሲያ መሳሪያዎችን አጠቃቀም የሚያሰለጥኑ እንደሆኑ ገልጻለች።
ወታደሮች በፈረንጆቹ 2020 እና 2021 ባካሄዱት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የያዙባት ማሊ ለረጅም አመታት ከእስላማዊ አማጺያን ጋር እየተዋጋች ትገኛለች
የሩሲያው ዋግነር ተዋጊ ቡድን በማሊ በነበረው ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት አስታወቀ።
የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ዋግነር በዛሬው እለት እንዳስታወቀው ቡድኑ እና የማሊ ወታደሮች ከቱአሬግ አማጺያን ጋር ባደረጉት ውጊያ ከባድ ኪሳራ አጋጥሟቸዋል።
ወታደሮች በፈረንጆቹ 2020 እና 2021 ባካሄዱት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የያዙባት ማሊ ለረጅም አመታት ከእስላማዊ አማጺያን ጋር እየተዋጋች ትገኛለች። ማሊ ግን በግዛቷ ያሉት የዋግነር ቅጥረኞች ሳይሆኑ ለወታሮቿ የሩሲያ መሳሪያዎችን አጠቃቀም የሚያሰለጥኑ እንደሆኑ ገልጻለች።
አማጺ ቡድኑ፣ ባለፈው ቅዳሜ እለት በድንበር አካባቢ በምትገኘው ቲንዙዋተን በተካሄደ ውጊያ ብረት ለበሽ ተሽከርካሪዎች፣ የጭነት መኪናዎች እና ታንከሮችን መያዙን ተናግሯል።
ዋግነር ባወጣው ያልተለመደ መግለጫ ወታደሮቹ ከማሊ ወታደሮች ጎን ሆነው ከሐምሌ 22-27 መዋጋታቸውን እና የዋግነር ተዋጊዎች በሰርጌ ሸቭቸንኮ ሲመሩ እንደነበር ጠቅሷል። ዋግነር እንደገለጸው የዋግነር ወታደሮች "ፖንድ ግሩፕ" የሚል ኮድ ተጠቅመዋል።
"በመጀመሪያው ቀን 'የፖንድ ግሩፕ' አብዛኛውን የእስላማዊ ታጣቂዎች ደምስሷል፤ ሌሎቹን አባሯል" ሲል ዋግነር በቴሌግራም ገጹ ገልጿል።
"ነገርገን የአሽዋማው ንፋስ ታጣቂዎቹ በድጋሚ እንዲሰባሰቡ እና ቁጥራቸውም ወደ አንድ ሺ ከፍ እንዲል አስቻላቸው።"
ዋግነር ተዋጊዎቹ በድጋሚ ታጣቂዎቹን በድጋሚ ማባረር ቢችሉም፣ ከፍተኛ ውጊያ ስለተካሄደ በመሀል በዋግነር ተዋጊዎች እና በማሊ ጦር ላይ ጉዳት መድረሱን አምኗል።
ከዋግነር ቡድን ባለፈው ሐምሌ 27 የተላከው መልእክት "ሶስታችን ቀርተናል፤ መዋጋታችንን እንቀጥላለን" የሚል ነበር።ዋግነር እንደገለጸው ሸቭቸንኮ ገድሏል።
የማሊ ጦር ባወጣው መግለጫ ሁለት ወታደሮቹ መገደላቸውን እና ሌሎች 10 የሚሆኑት መቁሰላቸውን ገልጿል። ጦሩ በመደበኛ ወታደራዊ ልምምድ ወቅት አንድ ወታደራዊ አውሮፕላኑ ባለፈው አርብ እለት ኪዳል አካባቢ እንደተጋጨበት ነገርግን በአደጋው የሞተ ሰው አለመኖሩን ተናግሯል።