የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ 7 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን አስታወቀ
አየርመንገዱ 577,746 የበረራ ሰአቶችን ማስመዝገቡን እና ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ19 በመቶ ጭማሪ አለው።
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ ይህ ትርፍ ከባለፈው ከመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል
የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ 7 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ 7.02 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ ይህ ትርፍ ከባለፈው ከመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል።
ትርፉ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ 402 ቢሊዮን ብር ይሆናል።
ስራ አስፈጻሚው እንደገለጹት አየርመንገዱ 577,746 የበረራ ሰአቶችን ማስመዝገቡን እና ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ19 በመቶ ጭማሪ አለው።
በበጀት አመቱ 17.1 ሚሊዮን መንገደኞችን ማመላለሱን የገለጸው አየርመንገዱ ከእነዚህ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆኑት አለምአቀፍ መንገደኞች ሲሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑን ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ናቸው ብሏል።
ይሁን እንጂ የአርመንገዱ የእቃ ጭነት ገቢው ግን ቅናሽ አሳይቷል።
አየር መንገዱ 54ሺ ቶን በላይ ጭነት ማጓጓዙን ገልጿል። አየርመንገዱ ከእቃ ጭነት ያገኘው ገቢ 1.65 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 8 በመቶ ቅናሽ ማሳነቱ ጠቅሷል።
ስራ አስፋጻሚው እንደገለጹት የኢትዮጵያ አየርመንገድ 125 አውሮፕላኖችን እንዲመረቱ ማዘዙን ተናግረዋል።