የዓለም ጤና ድርጅት ምንምእንኳን እናቶች በቫይረሱ ቢያዙም ጡት እንዲያጠቡ መክሯል
የዓለም ጤና ድርጅት ምንምእንኳን እናቶች በቫይረሱ ቢያዙም ጡት እንዲያጠቡ መክሯል
አለምአቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት እየተዘከረ ባለበት ወቅት፣ የአለም ጤና ድርጅት ምንምእንኳን እናቶች በኮሮና ቫይረስ ቢያዙም ልጆቻቸውን ጡት እንዲያጠቡ ጠይቋል፡፡ የድርጅቱ ዋና ሃላፊ ቴድሮስ አድሃኖም ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት ጡት ማጥባት ከኮሮና ተጋላጭነት ይበልጣል ብለዋል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠሩ ወይንም የተያዙ እናቶች ጡት ቢያጠቡ የሚበረታታ መሆኑን አስታውቋል፡፡የዘንድሮው አለም አቀፍ ጡት የማጥባት ቀን “ጡት ማጥባት ለጤና አለም” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት አለም ጤና ድርጅትና ዩኢሴፍ መንግስት ሴቶች ጡት የሚያጠቡበትን መንገድ ኢንዲያበረታቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ባለፈው ታህሳስ ወር በቻይና ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ መላውን አለም አዳርሶ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውስን አስካትሏል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያቀርበው ወርዶሜትር እንደዘገበው እስካሁን ወደ 700ሺ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲጠቁ፤ከ18 ሚሊዮን የሚልቁ መሆናቸውን አመልክቷል፡፡