ድርጅቱ ሪከርድ የሰበረ እለታዊ የኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር ሪፖርት አደረገ
በቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር አሜሪካ በ4 ሚሊዮን ሰዎች አለምን እየመራች መሆኑን ድርጂቱ አስታውቋል
በአለም ደረጃ እለታዊ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበ
በአለም ደረጃ እለታዊ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበ
የአለም ጤና ድርጅት በትናንትናው እለት 284196 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት ያደረገ ሲሆን ይህም በየቀኑ የሚያዙትን ሰዎች ቁጥር ክብረወስን ሰብሯል፡፡
እለታዊ የሞት መጠን ወደ 9753 ከፍ በማለቱ በየካቲት ወር ላይ ከተመዘገበው ከፍተኛ የሞት መጠን ቀጥሎ የሚጠቀስ ነው፡፡
የአለም ጤና ድርጅት በፈረንጆቹ ሀምሌ 18፤ 259848 ሰዎች መያዛቸውን ሪፖርት ባደረገበት ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ተብሎ ተመዝግቦ ነበር፡፡ በሰኔ ወር የነበረው 4600 አማካኝ እለታዊ የሞት መጠን፣ በሀምሌ ወር ወደ 5000 ከፍ ማለቱን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
የአለምጤና ድርጅት በአሜሪካ 69641ሰ ዎቸ፣በብራዚል 67860 ሰዎች፣ በህንድ 49310 ሰዎች እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ 13104 ሰዎች በኮሮና መያዛቸውን አስታውቋል፡፡ የደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ፔሩ በቅርብ የኮሮና ቫይረስ መረጃዋ ሲታይ በአንድ ቀን ብቻ 3000 የሞት መጠን በማስመዝገቧ፤የሀገሪቱ ጠቅላላ የሞት መጠን ወደ 17000 ደርሷል፡፡
ህንድ በፈረንጆቹ ሀምሌ17 አንድ ሚሊዮን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ሪፖርት በማድረግ ከአሜሪካና ከብራዚል በመቀጠል ሶስተኛ ሀገር ሆናለች፡፡ የጤና ባለሙያዎች ህንድ ከፍተኛ ተጠቂዎችን የምታስመዘግብበት ጊዜ ገና መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በብራዚል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን አልፏል፤ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በየቀኑ 40000 አዲስ በኮሮና የተያዙ ሰዎችን እያስመዘገበች ነው፡፡
በአራት ሚሊዮን የተጠቂዎች ቁጥር አለምን በአንደኝነት እየመራች ያለችው አሜሪካ፤ቫይረሱን ለመግታት እየሰራች ትገኛለች፡፡