በፈረንጆቹ 2020 በዓለም 243 ሚሊዮን ሴቶች ጾታዊ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተመድ በሪፖርቱ ገለጸ
“ጾታዊ ግንኙነት እንደማንኛውም ነገር ፈቃድ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው” ብሏል ሪፖርቱ
ጾታዊ ጥቃት ከተፈጸመባቸው ሴቶች 30 በመቶ የሚሆኑት ለአቅመ ሄዋን መሆናቸውን ሪፖርቱ ገልጿል
በዓለማችን 736 ሚልዮን ሴቶች -ቢያንስ ከሶስቱ አንድ ሴት ላይ- በትዳር አጋሮቻቸው፣ የቅርብ ዘመድ ወይም የሩቅ ሰው አማካኝነት ጾታዊ ጥቃት እንደሚያጋጥማቸው የተመድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በትዳር አጋር ወይም ፍቺ ከፈጸሙበት ቀድሞ የትዳር አጋር እንዲሁም የቅርብ ጓደኛ ጾታዊ ጥቃት ከሚፈጸምባቸው ሴቶች ፤30 በመቶ የሚሆኑት ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ሴቶች ናቸውም ነው የተባለው፡፡
ተመድ ባለፈው ወር ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከሆነ፤ 42 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች በአፍቃሪዎቻቸው ወይም በትዳር አጋሮቻቸው ጾታዊ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
በተለይም የኮሮና ወረርሺኝ ከተከሰተ ወዲህ በሴቶች ላይ የሚፈተመው ጾታዊ ጥቃት መጨመሩን በተመድ የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ፑምዚሌ ማላምቦ-ጉካ ገልጸዋል፡፡
ዳይሬክተሯ “ባለፈው ዓመት[2020 ዓ.ም]ብቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ 243 ሚሊዮን ሰቶች ከቅርብ አጋሮቻቸው ጸታዊ ጥቃት ተፈጽሞባቿል”ም ብሏል፡፡
ጾታዊ ጥቃት ከተፈጸመባቸው ሴቶች 40 በመቶ የሚሆኑት ሪፖርት ማድረጋቸውንና እገዛ መጠየቃቸውንም ዳይሬልተሯ ገልጿል፡፡
“ጾታዊ ፈቃድ” ሲባል ምን ማለት ነው?
በትዳር አጋር የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት ሲባል ከሴቷ ፈቃድ ዳጭ የሚደረግ ጾታዊ ግንኙነት እንደሆነ የሴቶች መብቶች ተሟጋቾች ይገልጻሉ፡፡
“ጾታዊ ፈቃድ” ሲባል አንዲት ሴት ራሷን በምታውቅበት ሰዓት ማለትም ፡[ኣልኮል ወይ ዕጽ ተጠቅማ ራሷን ባልሳተችበት] ሁኔታ የሚደረግ ግንኙነት ነው።
በተጨማሪም ከ18 ዓመት የእድሜ ክልል በታች የምትገኝ ሴት የምትወስነው ውሳኔ ይዞት የሚመጣ ውጤትን ያገናዘበ ነው ተብሎ ስለማይታመን ከህግ-አንጻር እንደ ጾታዊ ጥቃት ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል ዳሬክተሯ፡፡
ዳይሬክተሯ "ለእኔ በሴቷ የሚሰጠው ፈቃድ ሁሌ የሚታደስ ነው ፤ ለምሳሌ እንግዳ ቤትህ መጥቶ ቡና ላፍላልህ ወይ..? ሁለተኛ ልድገምህ ወይ …?" ብለን ነው የምንጠይቀው፡፡ ጾታዊ ግንኙነትም እንዲሁ ፈቃድ የሚያስፈልገው ነገር ነው" ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጅ፡ በተለይም በትዳር አጋሮች አማካኝነት ከሴቷ ፍላት ውጭ የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት የመናገር ባህል ባለሞኖሩ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታልም ይላሉ፡፡
“በሴቶች ላይ የሚደርስ ጾታዊ ጥቃት በማንኛውም ጊዜ ከጠዋት እስከ ማታ ልንታገለው የሚገባ ጉዳይ ነው፤ በተለይም በትዳር አጋር የሚፈጸም ጾታዊ አመጽ ለማስወገድ ትግል ይጠይቃል” ያሉት ደግሞ በአፍሪካ የተመድ የሴቶች ጉዳይ ምክትል ዳይሬክተር ዘቢብ ካቩማ ናቸው፡፡
ዘቢብ ካቩማ "ጾታዊ ጥቃት ምክንያታቸው ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፡፡ በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ይፈጸም ጥቃት ጥቃት ነው፤ በቃ! አመጽ ፈጽሞ መኖር የለበትም። በዳዮች እንዲጠየቁ ለማድረግ የወንዶች ሚናም ይጠበቃል ፤ እርስ በርሳችን ስለምንፈላለግ ችግሩን ለመፍታት በጋራ መስራት ግድ ነው" ሲሉም ተናግረዋል፡፡