የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የነበረችው አልጀሪያ የፍራንስ24ን የስራ ፈቃድ ሰረዘች
አልጀሪያ የፈረንሳይ ግዙፉ ሚዲያ ፍራንስ 24 የስራ ፈቃድ መሰረዟን ገልጻለች።
ሀገሪቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ፍርንስ 24 በተደጋጋሚ በግልጽ አልጀሪያን የሚያጠለሹ አሉታዊ ዘገባዎችን በመስራቱ እንደሆነ ገልጻለች።
የአልጀሪያ የኮሙንኬሽን ሚኒስቴር ከሁለት ወር በፊት ፍራንስ 24 ሚዲያ ስለ አልጀሪያ በሚያስተላልፋቸው ዘገባዎች ላይ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት እንደነበር ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
ፍራንስ 24 በበኩሉ ከአልጀሪያ መንግስት ውሳኔ መደነቁን ገልጾ ሚዲያው ስለ አልጀሪያ ነጻ እና ትክክለኛ ዘገባዎችን ሲሰራ መመቆየቱን ገልጿል።
በቀድሞ ቅኝ በገዛቻት ሀገራት ዋናው ሚያዋ የስራ ፈቃድ የተከለከለችው ፈረንሳይ ከአልጀሪያ ጋር ጥብቅ የሚባል ወዳጅነት እንዳላት ተገልጿል።
ይሁንና እስካሁን ፈረንሳይ በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም።
ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ወይም RSF) በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ተቋም አልጀሪያ ለጋዜጠኞች የማትመች አገር መሆኗን ጠቅሶ ከአንድ ዓመት በፊት ባወጣው ሪፖርት ከ180 ሀገራት ውስጥ በ146ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧት ነበር።
አልጀሪያ የእንደራሴዎች ምክር ቤት በማካሄድ ላይ ስትሆን ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑ መራጮች ድምጽ ከመስጠት መቆጠባቸውን ዘገባው አክሏል።