ታይዋን የጥንቃቄ አዋጅ ማወጇ ይታወሳል
የቻይና ተዋጊ አውሮፕላኖች ዛሬም የታይዋንን አየር ክልል ጥሰው መግባታቸው ተገለጸ።
ሲጂቲኤን እንዳስታወቀው 27 የቻይና ሱ35 ጄቶች የታይዋንን የአየር ክልል ጥሰው ገብተዋል። ቻይና የጦር ጀቶቿን ወደ ታይዋን መላኳ ዋሸንግተንንና ቤጅንግን ወደ ጦርነት እንዳያስገባ ተሰግቷል።
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ፤ ቻይና ግዛቴ በምትላት ታይዋን ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ቤጅንግ አውሮፕላኖቿን ወደ ታይዋን እየላከች ነው።
ቻይና የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን እንዳይሄዱ ስታስጠነቅቅ ብትቆይም ፔሎሲ ግን ታይዋን ቆይተው ተመልሰዋል።
ቻይና አውሮፕላኖቿን ወደ ታይዋን ማሰማራት የጀመረችው ከፔሎሲ ጉብኝት አስቀድሞ ነበር። አፈ ጉባዔዋ ታይዋንን ለቀው ከወጡ በኋላም የቻይ አውሮፕላኖች በታይዋን የአየር ክልል ላይ እየበረሩ ነው።
ቻይና፤የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ጦሯ “ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ ማስጠንቀቂያ ስትሰጥ ነበር።ከቻይና በተጨማሪም
ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያም የፔሎሲ ጉብኝትን ጉብኝት ኮንነው ነበር።
የቻይና የጦር አውሮፕላኖች ወደ ታይዋን በመግባታቸውና በፔሎሲ ጉብኝት ምክንያት ታይዋን ለሶስት ቀናት ከፍተኛ የውጊያ ጥንቃቄ ማወጇ ይታወሳል።
የቻይ ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዋንግ ይ ታይዋንን ነጻ ሀገር አድርጎ ማሰብ " ቀይ መስመር ማለፍ ነው" ብለዋል።