የቻይና ጦር የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ መሆኑን ገለፀ
ጦሩ የፔሎሲን ጉብኝት ተከትሎ ከባድ ወታደራዊ የአፀፋ እርምጃ ሊወስድ መሆኑን አስታውቋል
የአሜሪካ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ጉብኝት የቻይናን ዛቻ ወደጎን ትተው የታይዋን ጉብኝታቸውን ጀምረዋል
የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር የአፀፋ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታወቀ።
የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ወ ዩ ኪያን፤ የቻይና ጦር የሀገሪቱን ሉአላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ነው ብለዋል።
ቃል አቀባዩ የአሜሪካ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ የቻይና አካል በሆነችው ታይዋን ክልል ለጉብኝት መግባታቸውን ተከትሎ የቻይና ጦር በተመረጡ ኢላማዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።
የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሲ ሌሎሲ ታይዋንን ጨምሮ አምስት የእስያ ሀገራትን ጉብኝት መጀመራቸውን ተከትሎ ዓለም አይኑ ታይዋን ላይ አርፏል።
የአሜሪካዋ አፈጉባዔ የጉብኝታቸው አካል ወደሆነችው ታይዋን በዛሬው እለት ገብተዋል።
ቻይና በአሜሪካ ፖለቲካ ሶስተኛው የስልጣን ባለቤት እየሆኑት ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቷን ተከትሎ በሩቅ ምስራቅ ውጥረት ነግሷል።
አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋን መድረሳቸውን ተከትሎም የቻይና ሱ35 ጄቶች የታይዋንን የአየር ክልል ጥሰው መግባታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ቻይና፤የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ጦሯ “ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ”ቻይና ማስጠንቀቂያ አስተላልፋ እንደነበረ ይታወሳል።