ፖለቲካ
በማሊ በፈረንጆቹ 2021 በተፈጸመ ጥቃት 28 የተመድ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ተገድለዋል
በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ በማሊ የሰላም አስከባሪ ልኡክ የጥቃት ቁጥሩ ጨምሯል
የተመድ ሚሽን በማሊ በፈረንጆቹ 2021፣13ሺ ጥበቃዎችንና ንጹሃንን ለማዳን 100 ዘመቻዎችን ማካሄዱን አስታወቀ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) እንደገለጸው በፈረንጆቹ 2021 በተፈጸመ ጥቃት 28 የተመድ ሰላም አስከባሪዎች መገደላቸውንና ሌሎች 165 መቁሰላቸውን ተመድ አስታውቋል፡፡
የተመድ መልቲ ናሽናል ኢንተግሬትድ ስታቢላይዜሽን ሚሽን ሃላፊ ኢል ጋሲም ዋኔ ከግማሽ በላይ የሚሆነት የሞትና የመቁሰል አደጋዎች የተፈጸሙት በፈረንጅ ቁሶች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ ዋኔ ገለጻ የተመድ ሚሽን በዚህ አመት 13ሺ ጥበቃዎችንና ንጹሃንን ለማዳን 100 ዘመቻዎችን አካሂዷል፡፡ ዋኔ ህይወታቸውን ላጡ 8 ሰላም አስከባሪዎች የመታሰቢያ ፕሮግራም መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ በማሊ የሰላም አስከባሪ ልኡክ የጥቃት ቁጥሩ ጨምሯል ብለዋል፡፡
በፈረንጆቹ ታህሳስ፣ 8 የሰላም አስከባሪዎች ሲገደሉ ሌሎች ሶስት ሰዎች ቆስለዋል፤አደጋው የተከሰተው የልኡኩ የሎጅስቲክ ተሽከርካሪ በፈንጅ በተመታበት ጊዜ ነው፡፡