በአፍሪካ ቀንድ በተከሰተው ድርቅ ሶስት ሚሊዮን የቤት እንስሳት ሞቱ
ተመድ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ በድርቅ የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት ገንዘብ አሰባሰበ
በአፍሪካ ቀንድ በተከሰተው ድርቅ የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት ተመድ ባካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ 1 ነጥብ 39 ቢሊዮን ዶላር ሰበሰበ
በስዊዘርላንድ ጀኔቫ በተካሄደው በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ 1 ነጥብ 39 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
ይህ ገንዘብ በኢትዮጵያ ፣ኬንያ እና ሶማሊያ በድርቅ የተጎዱ ሰዎችን ለመደገፍ ይውላል ተብሏል።
በዚህ ዓመት በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተው ድርቅ ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ ያልታየ እንደሆነ የዓለም ምግብ ድርጅት ፋኦ ገልጿል።ይህ ድርቅ በሶማሊያ ስድስት አካባቢዎች ባስከተለው ጉዳት ረሀብ ተከስቷል ተብሏል።
በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ለአራት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ያልዘነበ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ ጉዳት ሊዳረጉ ችለዋል።
ድርቁ ከሰዎች ጉዳት ባለፈም ከሶስት ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳት የሞቱ ሲሆን ይህም በተለይም የምግብ ደህንነትን የከፋ እንዲሆን አድርጎታልም ተብሏል።
ላለፉት 40 ዓመታት ያልታየ ድርቅ በአፍሪካ ቀንድ እንደተከሰተ የተገለጸው ይህ ድርቅ በሶማሊያ 6 ሚሊዮን በኬንያ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን እንዲሁም በኢትዮጵያ 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸውል።