ፖለቲካ
ኤምባሲውን ዒላማ አድርገው ነበር የተባሉ 3 ሮኬቶች ባግዳድ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አቅራቢያ ማረፋቸው ተነገረ
ሆኖም የሚሳኤል ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመ የተገለጸ ነገር የለም
በጥቃቱ የደረሰ አካላዊ ጉዳት የለም
ኤምባሲውን ዒላማ አድርገው ነበር የተባሉ 3 ሮኬቶች ኢራቅ ባግዳድ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አቅራቢያ ማረፋቸው ተነገረ፡፡
ሮኬቶቹ ዛሬ ረፋድ በኤምባሲው አቅራቢያ ማረፋቸውን የኢራቅ የደህንነት ምንጮች አረጋግጠዋል።
የፈረንሳይ የዜና ወኪል የደህንነት ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ሦስቱ ሮኬቶች ዛሬ ረፋድ ላይ የወደቁት በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ አረንጓዴ ዞን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
አሜሪካ፤ ህወሓት ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች መቃረቡን እንዲገታ ጥሪ አቀረበች
አረንጓዴ ዞን የአሜሪካ ኤምባሲ እና ሌሎች የሃገሪቱ መንግስት ቢሮዎች የሚገኙበት ነው፡፡
በኢራቅ ከሰሞኑ የህግ አውጭዎች ምርጫ ተካሂዶ ነበር፡፡ የምርጫውን ውጤት አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቃውመዋል፡፡ የሮኬት ጥቃቱ ይህንኑ ተከትሎ መፈጸሙ ነው የተነገረው፡፡
ሆኖም ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመ የተገለጸ ነገር የለም፡፡ በጥቃቱ የደረሰ አካላዊ ጉዳት አለመኖሩም ተገልጿል፡፡