“የሱዳን ሽግግር መንግስትን በኃይል መቀየር የአሜሪካን ድጋፍ ያሳጣል”- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ
ዋሽንግተን፤ “የሽግግር መንግስቱ በወታደራዊ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተቀባይነት የለውም” ብላለች
አሜሪካ፤ የሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ እንደሚያስጨንቃት ገልጻለች
የሱዳን ሽግግር መንግስትን በኃይል ለመቀየር መሞከር፤ ዋሸንግተን ለካርቱም የምታደርገውን ድጋፍ ሊያሳጣ እንደሚችል በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው በይፋዊ የትዊተር ገጹ እንዳሰፈረው በሱዳን ያለውን የሽግግር መንግስት በኃይል መቀየር ተቀባይነት የለውም፡፡
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን፤ ሀገራቸው በሱዳን ያለው ፖለቲካዊ ለውጥ እንደሚያሳስባት አስታውቀዋል፡፡
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር መንግስት በወታደራዊ ቁጥጥር ስር መዋሉን አስመልክቶ አሜሪካ ሁኔታውን በከፍተኛ ሁኔታ እየተከታተለችው መሆኑንም ልዩ መልዕክተኛው ገልጸዋል፡፡
“በቁም እስር ላይ ናቸው” የተባሉት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደማይታወቅ ቦታ መወሰዳቸው እየተነገረ ነው
በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ “የሱዳን የሽግግር መንግስት ሲቪል አመራሮች በወታደሩ ቁጥጥር ስር መዋላቸው በወታደራዊ እና በሲቪል አመራሮች የተደረገውንና የሽግግር መንግስቱ የሚመራበትን ስምምነት የሚጥስ እና ከሱዳን ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ምኞትና ፍላጎት ጋር የሚቃረን” እንደሆነ ገልጿልቢሮው፡፡
በመሆኑም የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር መንግስቱ በወታደራዊ ቁጥጥር ስር መዋሉን ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል፡፡
ፌስቡክ በሱዳን የሚገኙ ፌክ አካውንቶችን መዝጋቱ አስታወቀ
በሽግግር መንግስቱ ላይ በኃይል የሚደረጉ ለውጦች የአሜሪካን እርዳታ አደጋ ላይ እንደሚጥሉ አሜሪካ በተደጋጋሚ ማሳሰቧንም ዋሸንግተን ገልጻለች፡፡
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ትናንትና እና ከትናንት በስቲያ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ እና ከሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ሊቀመንበር አብደል ፋታህ አልቡርሃን ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡