በማሊ የተ.መ.ድ. ዋና ጸኃፊ ልዩ ተወካይ ማሃመት ሳሌህ አናዲፍ ክስተቱን “የቡከኖች ድርጊት” በማለት በጽኑ አውግዘውታል
በማሊ የተ.መ.ድ. ዋና ጸኃፊ ልዩ ተወካይ ማሃመት ሳሌህ አናዲፍ ክስተቱን “የቡከኖች ድርጊት” በማለት በጽኑ አውግዘውታል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተ.መ.ድ.) በማሊ የሁሉን አቀፍ ሰላም ማስፈን ልኡክ በትናንትናው እለት እንዳረጋገጠው መደበኛ በሆነ የአሰሳ ስራ ላይ የነበሩ ሶስት የሰላም አስከባሪዎቹ በሰሜን ማሊ በአጉልሆክ አቅራቢያ በፈንጅ መገደላቸውን አስታውቋል፡፡
ልኡኩ ባወጣው መግለጫ ሌላ አራት ሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ እንደተጎዱና በአሁኑ ወቅት ህከምና እየተደረገላቸው መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በማሊ የተ.መ.ድ. ዋና ጸኃፊ ልዩ ተወካይና የልኡኩ ኃላፊ ማሃመት ሳሌህ አናዲፍ ክስተቱን “የቡከኖች ድርጊት” በማለት በጽኑ አውግዘውታል፤ አላማውም የልኡኩን እንቅስቃሴ ለማሽመድመድ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
አናዲፍ “ሁሉንም ጥረቶች በማቀናጀት ለእነዚህ ሽብር ድርጊቶች ተጠያቂ የሆኑ አካትን ለይተን እንይዛለን፣ በፍትህ ፊት ለሰሩት ወንጅል መልስ ይሰጣሉ“ ብለዋል፡፡
ልኡኩ ወደ ማሊ የተላከው በፈረንጆቹ 2013 ነበር፡፡ የልኡኩ አላማም በማሊ ያለውን የፖለቲካ ሂደት ለመርዳት አንደሆነ ተነግሯል፡፡