ፕሬዘዳንት ፑቲን ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ሜዳሊያ ሸለሙ
ከ4700 በላይ የሚሆኑ የሶቬት ወታደሮች በፈረንጆቹ 1945 ኮሪያን ነፃ ለማውጣት በተደረገው ጦርነት ሞተዋል
ከ4700 በላይ የሚሆኑ የሶቬት ወታደሮች በፈረንጆቹ 1945 ኮሪያን ነፃ ለማውጣት በተደረገው ጦርነት ሞተዋል
ለኮሪያ ነፃነት ሲሉ የሞቱ የሶቬት ወታደሮች መቃብር በጥሩ ሁኔታ በመያዙ ፑቲን ለኪም ጆንግ ኡን የማስታወሻ ሜዳሊያ ሸለሙ
ሩሲያ በሁለተኛው የአለም ጦርነት የጀርመኑን ናዚ በማሸነፍ ድል የተቀዳጀችበትን 75ኛ የመታሰቢያ አመት ስታከብር ፕሬዘዳንት ፑቲን ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የማስታወሻ ሜዳሊያ ሽልማት አበርክተዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያውን ሴንትራል ኒውስ ኤጀንሲን ጠቅሶ ሲጂቲኤን እንደዘገበው የድሉን 75ኛ መታሰቢያ አመትና የኪምን የማስታወሻ ሽልማት ዝግጅት ማንሱዴ በተባለ የስብሰባ አዳራሽ መካሄዱን ዘግቧል፡
የማስታወሻ ሜዳሊያው በሰሜን ኮሪያ የሩሲያ አምባሳደር በሆኑት አልክሳንደር ማታስጎራ ለኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪ ሰን ግዎን ተሰጥቷል፡፡
አምባሳደሩ ከፑቲን የተላከውን ሜዳሊያና የምስክር ወረቀት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሪ ሰን አስረክበዋል
ምንምእንኳን ሰሜን ኮሪያ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ መኖሩን ሪፖርት ባታደርግም፤ በስነስርአቱ ወቅት የሰሜን ኮሪያና የሩሲያ ባለስልጣናት የፊት መሸፈኛ ጭምብል አድርገው ታይተዋል፡፡
የሩሲያ ኢምባሲ እንዳስታወቀው ኪም ጆንግ በሰሜን ኮሪያ ምድር የሞቱትንና የተቀበሩትን የሶቬት ዜጎች የመቃብር ቦታ በመጠበቅና በመንከባከብ በሩሲያ ፕሬዘዳንታዊ አዋጅ መሰረት ሜዳሊያው ተበርክቶላቸዋል፡፡
ከሽልማቱ በኋላ የሩሲያ አምባሳደርና የሰሜን ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረዘም ላለ ጊዜ ውይይት አድርገዋል፤ በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል በፈረንጆቹ 2019 የተደረሰውን ስምምነት ለመተግበር ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡
በሰሜን ኮሪያ 1375 የሩሲያ ወታደሮች የተቀበሩበት 11 የጅምላ መቃብሮችና 345 የሚሆኑ የግለሰብ መቃብሮች መኖራቸውን ኢምባሲው ገልጿል፡፡
በፈረንጆቹ 1945፣ ከ4700 በላይ የሚሆኑ የሶቬት ወታደሮች ኮሪያን ነፃ ለማውጣት በተደረገው ጦርነት ቆስለው ሞተዋል፡፡ አሁን ላይ በፒዮንግያንግ ቁልፍ ከሚባሉ መገለጫ ቦታዎች፤ ሰሜን ኮሪያን በፈረንጆቹ 1945 ከጃፖን ወረራ ነፃ ለማውጣት በተደረገው ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡ የሶቬት ወታደሮች የተሰራው ማስታወሻ ሀውልት ነው፡፡
የኮሪያ ባህረሰላጤ ከፈረንጆቹ 1910 እስከ 1945 በጃፓን ቅኝ ግዛት ስር ነበር፡፡ሰሜን ኮሪያና ሩሲያ ከፈረንጆቹ 1940 ጀምሮ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት እያደረጉ ቆይተዋል፡፡