የ80 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣኔን በፈቃደኝነት እለቃለሁ አሉ
የ80 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣኔን በፈቃደኝነት እለቃለሁ አሉ
የ80 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ የሆኑት የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ ከአሁን በኋላ “አቅም የለኝም፤ስልጣኔን በሚመጣው ሐምሌ እለቃለሁ” ብለዋል፡፡
ታባሜ በፈረንጆቹ 2017በቀድሞ ሚስታቸው ግድያ ተሳትፈዋል ተብለው ተጠርጥረው ስልጣን እንዲለቁ ከፍተኛ ግፊት ሲደረግባቸው እንደነበረ ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
የታባኔ የስልጣን ዘመን በፈረንጆቹ 2022 የሚያበቃ ሲሆን በፈቃደኝነት ስልጣናቸውን ይለቃሉ፡፡
ታባኔ እድሜያቸው መግፋቱ ከስልጣን ለመልቀቅ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡
ታባኔ “የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስራ አካላዊ ጥንካሬ ይጠይቃል፡፡ በእድሜ መግፋት ምክንያት አንደ በፊቱ ጠንካራ አይደለሁም፡፡ በዚህም ምክንያት በፍቃደኝነት ስልጣኔን ለቅቄ፣ በሌሴቶ ህግ መሰረት ለሚረከበው መንግስት አስረክባለሁ” ብለዋል፡፡