ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የፕሬዘዳንት ሙታሪካን ምርጫ ማሸነፍ ውድቅ ያደረገበትን ውሳኔ አጸና
የህገመንግስቱ ፍርድቤት “መጠነሰፊ፣ስልታዊና አደገኛ” የሆኑ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች ተስተውለው ነበር ብሏል
የማላዊ የህገመንግስት ፍርድቤት “መጠነሰፊ፣ስልታዊና አደገኛ” የሆኑ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች ተስተውለውበታል ያለውን የምርጫ ውጤት ውድቅ አደረገ
የማላዊ የህገመንግስት ፍርድቤት “መጠነሰፊ፣ስልታዊና አደገኛ” የሆኑ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች ተስተውለውበታል ያለውን የምርጫ ውጤት ውድቅ አደረገ
የማላዊ ጠቅላይ ፍርድቤት ቀድም ብሎ የፕሬዘዳንት ፒተር ሙታሪካን ምርጫ በጠባብ ውጤት ማሸነፍ ውድቅ ያደረገበትን ውሳኔ አጽንቷል፡፡
የሀገሪቱ ድጋሚ ምርጫ በመጭው ሀምሌ ወር እንዲካሄድ እቅድ ተይዞለታል፡፡
የሀገሪቱ የህገመንግስት ፍርድቤትም ባለፈው የካቲት ወር “መጠነሰፊ፣ስልታዊና አደገኛ” የሆኑ ትክክል ያልሆኑ አሰራሮች በመስተዋላቸው፤ የሙታሪካን ድጋሚ ወደ ስልጣን ሊመልስ የሚችለውን ምርጫ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ፕሬዘዳንት ሙታሪካና የምርጫ ኮሚሽን ፍርድቤቱ ያሳለፈውን ውሳኔ ይግባኝ ብለው ነበር፡፡
ጠቅላይ ፍርድቤቱ በትናንትናው እለት ባሳለፈው ውሳኔ እንደገለጸው በርካታ የህግ ጥሰቶች የማላዊን ምርጫ ኮሚሽን ኃላፊት ላይ ተጽእኖ አሳድረውበታል፤የመራጮችንም መብት በእጅጉ የጎዳ ነው፡፡ የትኛውም እጩ አብላጫ ድምጽ አላገኘም”ብሏል፡፡
በተጨማሪም ፍርድቤቱ ምርጫ ቦርድ ይግባኝ ማለትም አልነበረበትም፤ ይህን ሲያደርግ ወገንተኛኝነት ይዞ አንደነበረ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
ማላዊ በውጭ እርዳታ ላይ ጥገኛ የሆነች ሀገር ስትሆን ድርቅም በተደጋጋሚ እንደሚጎበኛት ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በፈረንጀቹ ከ2014 ጀምሮ ስልጣን የያዙት የቀድሞው የህግ ፕሮፌሰር በመጀመሪ አምስት አመት የስልጣን ዘመናቸው የመሰረተ ልማት ማሻሻያ ቢያደርጉም፤ ተችዎች ግን መስናን መከላከል አልቻሉም እያሉ ይከሷቸዋል፡፡