በቀን ከ30 ደቂቃ በላይ ስልክ ማውራት ለደም ግፊት እንደሚዳርግ ተመራማሪዎች ገለጹ
ዕለታዊ የስልክ ልውውጥን መቀነስ በደም ግፊት የመጠቃት እድልን ይቀንሳል ተብሏል
ተመራማሪዎች እንዳሉት ረዥም ሰዓት የሞባይል ስልክ የሚደውሉ ሰዎች ለደም ግፊት የበለጠ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል
በቀን ከ30 ደቂቃ በላይ ስልክ ማውራት ለደም ግፊት እንደሚዳርግ ተመራማሪዎች ገለጹ።
በየጊዜው እየዘመነ የመጣው የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎትን በማቀላጠፍ ህይወትን የበለጠ ቀላል እያደረገ ይገኛል።
ይሁንና አሁን በወጣ ጥናት በቀን ከ30 ደቂቃ በላይ የሞባይል ስልክ የሚደውሉ ወይም የሚቀበሉ ሰዎች ለደም ግፊት ተጋላጭ ናቸው ተብሏል።
የደቡባዊ ቻይና ህክምና ተመራማሪዎች የሰዎችን ዕለታዊ የስልክ ልውውጥ ከደም ግፊት ጋር ያለውን ዝምድና መርምረዋል ሲል ዴይሊሜይል ዘግቧል።
በዚህ ምርመራም በየቀኑ አንድ ሰዓት መደበኛ የስልክ አገልግሎት የሚያገኙ ወይም የሚቀበሉ ሰዎች ለደም ግፊት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
በዚህ ጥናት መሰረትም ከግማሽ ሰዓት ጀምሮ በየቀኑ የሚደውሉ አልያም የሚቀበሉ ሰዎች ለደም ግፊት እንደሚገለጡ ተመራማሪዎቹ አክለዋል።
ተመራማሪዎቹ በብሪታንያ በሚኖሩ 200 ሺህ ወጣቶችን በጥናታቸው ያሳተፉ ሲሆን ጥናቱ የወጣቶቹን ዕለታዊ የስልክ አጠቃቀም እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።
ለ12 ዓመታት በተደረገው በዚህ ጥናት መሰረትም በጥናቱ ከተሳተፉት ውስጥ 30 ደቂቃ እና ከዛ በላይ ዕለታዊ የስልክ ልውውጥ የሚያደርጉ ወጣቶች ከ12 በመቶ በላይ ለደም ግፊት ተጋልጠው ተገኝተዋል።
አነስተኛ የስልክ ልውውጥ የሚያደርጉ ሰዎች ደግሞ ለደም ግፊት የመጠቃት ያላቸው እድል አነስተኛ ሆኖ መገኘቱንም ይሄው ጥናት አመላክቷል ተብሏል።
በሳምንት ስድስት ሰዓት የሚጠቀሙ ሰዎች ደግሞ ለደም ግፊት በ25 በመቶ የተጋለጡ ሆነው እንደተገኙም ተገልጿል።
በብሪታንያ 14 ሚሊዮን ዜጎች የደም ግፊት የተገኘባቸው ሲሆን በስልካቸው ላይ የሚገኘው የራዲዮ አክቲቭ ሀይል የደም ዝውውር ላይ አሉታዊ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተመራማሪዎች አክለዋል።