እስካሁን የኮሮና ቫይረስ በተገኘባቸው 36 የአፍሪካ ሀገራት 804 የቫይረሱ ተጠቂዎች ተለይተዋል
እስካሁን የኮሮና ቫይረስ በተገኘባቸው 36 የአፍሪካ ሀገራት 804 የቫይረሱ ተጠቂዎች ተለይተዋል
የአፍሪካ የበሽታ መከላከል ማእከል ዛሬ ባወጣው መረጃ እንዳስታወቀው በ36 ሀገራት በድምሩ 804 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ይገኛሉ፡፡ ቫይረሱ ከተከሰተባቸው ሀገራት በአምስቱ 19 ሰዎች ሞተዋል፡፡
በስምንት ሀገራት ደግሞ ባጠቃላይ 84 ሰዎች አገግመዋል፡፡ 256 የበሽታው ታማሚዎች የሚገኙባት ግብጽ በተጠቂዎች ቁጥር ስትመራ ደቡብ አፍሪካ በ150፣ አልጄሪያ በ82 ይከተላሉ፡፡
hገራት (36) ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር (795)፡ አልጄሪያ (82) ፣ ቤኒን (2) ፣ ቡርኪና ፋሶ (27) ፣ ካሜሩን (21) ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፓብሊክ (1) ፣ ቻድ (1) ፣ ኮንጎ (1) ፣ ኮትዲቮር (6) ፣ ጅቡቲ (1) ፣ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ (18) ፣ ግብፅ (256) ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ (4) ፣ ኢስዋቲኒ (1) ፣ ኢትዮጵያ (9) ፣ ጋቦን (3) ፣ ጋምቢያ (1) ፣ ጋና ( 7) ፣ ጊኒ (2) ፣ ኬንያ (7) ፣ ላይቤሪያ (2) ፣ ሞሪሺየስ (7) ፣ ሞሪታኒያ (2) ፣ ሞሮኮ (63) ፣ ናሚቢያ (2) ፣ ኒጀር (1) ፣ ናይጄሪያ (12) ፣ ሩዋንዳ ( 11) ፣ ሴኔጋል (38) ፣ ሲሸልስ (6) ፣ ሶማሊያ (1) ፣ ደቡብ አፍሪካ (150) ፣ ሱዳን (1) ፣ ታንዛኒያ (6) ፣ ቶጎ (1) ፣ ቱኒዚያ (39) ፣ ዛምቢያ (2) ፣ ሌሎች ግዛቶች ማዮቴ (በአፍሪካ ዳርቻ የህንድ ውቂያኖስ ላይ የሚገኝ የፈረንሳይ ግዛት) (1) ፣ ሪዩኒየን (በአፍሪካ ዳርቻ የህንድ ውቂያኖስ ላይ የሚገኝ የፈረንሳይ ግዛት) (9)
ሞት ያስተናገዱ ሀገራት (5)፣ የሟቾች ብዛት (19) አልጄሪያ (8) ፣ ቡርኪና ፋሶ (1) ፣ ግብፅ (7) ፣ ሞሮኮ (2) ፣ ሱዳን (1)
የኮሮና ታማሚዎች ያገገሙባቸው ሀገራት (8)፣ ያገገሙ ሰዎች ብዛት (84): አልጄሪያ (32) ፣ ካሜሩን (2) ፣ ግብጽ (28) ፣ ሞሮኮ (2) ፣ ናይጄሪያ (2) ፣ ሴኔጋል (5) ፣ ደቡብ አፍሪካ (12) ፣ ቱኒዚያ (1)
ከተጠቀሱት ስምንት ሀገራት በተጨማሪ በኢትዮጵያ 4 ታማሚዎች ማገገማቸውን እና ሁለት ታማሚዎች ደግሞ በመልካም ጤንነት ላይ ሆነው ህክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወቃል፡፡