ግብጽ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አቋሟን ለማስረዳት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ 6 የአፍሪካ ሀገራት ላከች፡፡
ግብጽ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አቋሟን ለማስረዳት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ 6 የአፍሪካ ሀገራት ላከች፡፡
ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ አቋሟን ለማስረዳት ግብጽ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የተመራ ልዕክ ወደ አፍሪካ መላኳን አስታወቀች፡፡
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ የተመራው ልዑክም የመጀመሪያ መዳረሻውን በቡሩንዲ መዲና ቡጁምብራ አድርጓል፡፡ በሀገሪቱም ከፕሬዝዳንት ፔሬ ንኩሩንዚዛ ጋር ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ ጭምብል እንደለበሱ በነበራቸው ቆይታ በግድቡ ዙሪያ ቡሩንዲ ለግብጽ አቋም ድጋፍ እንድትሰጥ ጠይቀዋል፡፡
ሳሚ ሽኩሪ በአፍሪካ ቆይታቸው ደቡብ አፍሪካ፣ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ፣ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ደቡብ ሱዳንና ኒጀር ያቀናሉ ተብሏል፡፡ በቆይታቸውም በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከፕሬዚዳንቱ የተላከ መልዕክትን ያደርሳሉ ተብሏ፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ለዓረብ ለአውሮፖ ሃገራት ከፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ የተላከ መልዕክትን ማድረሳቸው ይታወሳል፡፡