እስራኤል በጦርነቱ እስካሁን ስንት ወታደሮቿን አጣች?
እስራኤል በዛሬው እለት የሀማስ የማዘዣ ጣቢያ ሆኖ አገልግሏል ያለችውን ግዙፉን የጋዛ ሆስፒታል አል ሽፋን ወርራለች
የተገደሉ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 368 መድረሱ ተገልጿል
በእስራኤል- ሀማስ ጦርነት የተገደሉ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር እስካሁን 368 ደርሷል።
ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ከባለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ የተገደሉ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 368 መድረሱን እስራኤል ጦር ይፋ አድርጓል።
ሀማስ በትናንትናው ውጊያ ዘጠኝ የእስራኤል ወታደሮችን መግደሉን እና 22 የሚሆኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ማውደሙን አስታውቋል።
ነገርግን የእስራኤል ጦር በትናንትናው እለት በጋዛ ሰርጥ በተካሄደው ውጊያ የተገደሉት ሁለት ወታደሮች ብቻ መሆናቸውን ገልጿል።
የእስራኤል ጦር ተገድለዋል ያላቸውን ወታደሮች ሰም ዝርዝርም ይፋ አድርጓል።
ጦሩ እንደገለጸው ጦርነቱ ከተጀመረበት ጥቅምት ጀምሮ ከተገደሉት ወታደሮች ውስጥ 49 የሚሆኑት እስራኤል በጋዛ ወረራ ከፈጸመች በኋላ የተገደሉ ናቸው።
የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት የተቀሰቀሰው ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ በ50 አመታት ውስጥ እጅግ ከባድ የተባለ ጥቃት በማድረሱ ምክንያት ነው። ይህን ጥቃት ተከትሎ ሀማስን ከምድረ ገጹ አጠፋለሁ ያለችው እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት ጋዛ ከተማ በመግባት ሀማስ ይኖርበታል ብላ የምታስበውን ቦታ ሁሉ እያሰሰች ነው።
እስራኤል በዛሬው እለት የሀማስ የማዘዣ ጣቢያ ሆኖ አገልግሏል ያለችውን ግዙፉን የጋዛ ሆስፒታል አል ሽፋን ወርራለች።
በጦርነቱ በጋዛ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ በመፈጠሩ ምክንያት ተመድ እና በርካታ ሀገራት የተኩስ አቁም ጥሪ ቢያቀርቡም እስራአል ፈቃደኛ አልሆነችም።