በጋዛ እያረገን ያለውን ቤሩት ውስጥ ማድረግ እንችላለን- የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር
ዮአቭ ጋላንት “ሄዝቦላህ ሊባኖስን ወደ አይቀሬ ጦርነት እያስገባ ነው” ብለዋል
“ሄዝቦላህ ስህተት እየሰራ ነው፤ ዋጋ የሚከፍሉት ግን በመጀመሪያ ደረጃ የሊባኖስ ዜጎች ናቸው” ብለዋል
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የሊባኖሱን ሄዝቦላህ ከፍተኛ ስህተት እየሰራ ነው ሲል አስጠነቀቀ።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ለሀገሪቱ ሰራዊት አባላት ባደረጉት ንግግር፤ በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ ሊባኖስን ወደ ጦርነት ሊያስገባ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
ዮአቭ ጋላንት በንግግራቸው፤ “ሄዝቦላህ ሊባኖስን ወደ አይቀሬ ጦርነት እያስገባ ነው፤ ይህ ደግሞ ትልቅ ስህተት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
"ሄዝቦላህ ስህተት እየሠራ ነው” ያሉት ዮአቭ ጋላንት “በሄዝቦላህ ስህተት ዋጋ የሚከፍሉት በመጀመሪያ ደረጃ የሊባኖስ ዜጎች ናቸው” ብለዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ፤ “በጋዛ እያረገን ያለውን ቤሩት ውስጥ ማድረግ እንችላለን” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
በኢራን እንደሚደገፍ የሚነገርለት እና በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰው ሄዝቦላህ ቡድን እስራኤል ከሃማስ ጋር ጦርነት ከጀመረች ወዲህ በእስራኤል ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን ሲሰነዝር ቆይቷል።
ይህንን ተከትሎም እስራኤል በጦር ጄቶች እና በመድፍ በሊባኖስ ድንበር ላይ የሚገኙ የሄዝቦላህ ይዞታዎችን ስትመታ ነበር።
የሄዝቦላህ ቡድን መሪ በትናንታው እለት ቡድኑ አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅሞ በእስራኤል ውስጥ አዳዲስ ኢላማዎችን መምታቱን ተናግረዋል።
በደቡብ ከሉል ያለው የሄዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ከንፍ ጠላት ባላት እስራኤል ላይ ጥቃት መሰንዘሩን እንደሚቀጥልም ቡድኑ ቃል ገብቷል።