እስራኤል በጋዛ በምታደርገው ጦርነት ምክንያት ሀገራት አምባሳደሮቻቸውን በመጥራት በእስራኤል ላይ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል
እስራኤልን በመቃወም አምባሳደሮቻቸውን የጠሩ ሀገራት እነማን ናቸው?
እስራኤል በጋዛ በምታደርገው ጦርነት ምክንያት በርካታ ሀገራት አምባሳደሮቻቸውን በመጥራት በእስራኤል ላይ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።
ሀማስ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ሳምንት ላይ ያልተጠበቀ እና ከባድ የተባለ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ እስራኤል የሀማስ ይዞታ በሆነችው ጋዛ ላይ የማያባራ ጥቃት እያደረሰች ነው።
ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የሰብአዊ ሁኔታው ያሳሰባቸው ቢያንስ ስምንት ሀገራት በእስራኤል የነበሯቸውን አምባሳደሮች መጥራታቸውን አለፍአቀፍ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።
እስራኤል በጋዛ እየወሰደችው ያለው መጠነሰፊ ጥቃት እንደአሜሪካ ባሉ አጋሮቿ ሁለንተናዊ ድጋፍ ቢቸረውም፣ የአረብ ሀገራትን ጨምሮ በርካቶች ተኩስ እንድታቆም በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።
ብዙ የአለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመው ጥቃት በቀጣናው የሰብአዊ ቀውስ ያስከትላል ሲሉ አስተጠንቅቀዋል።
ይህን በመቃውም ስምንት ሀገራት አምባሳደሮቻቸውን ከእስራኤል ጠርተዋል።
የደቡብ አሜሪካዋ ቦልቪያ አምባሳደሯን በማስወጣት የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።