የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በምን ጉዳይ ላይ ተወያይተው ውሳኔ ያሳልፋሉ?
የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ "የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/15/252-140015-whatsapp-image-2025-02-15-at-11.43.32-am_700x400.jpeg)
የህብረቱ ጉባዔ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ምርጫ እንደሚያካሄድም ይጠበቃል
38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
"የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን" በሚል መሪ ቃል እየተካደ ያለው ገባዔው ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር እና ውሳኔዎችን እንደሚሳልፍ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ የማካካሻ ፍትህ፣ አህጉራዊ ሰላምና ደህንነት ውይይት የሚደረግባቸው አጀንዳዎች መካከለ ናቸው፡፡
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አፈጻጸምና አህጉራዊ የንግድና ኢኮኖሚ ትስስር፣ ግብርናና የአየር ንብረት ለውጥ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ ስርዓተ ጾታና ወጣቶችን ማብቃት እንዲሁም የተቋማት አደረጃጀቶች ላይም ጉባኤው ይወያያል።
አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ለማግኘት እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተም ህብረቱ የሚወያይበት እንደሚሆን ይፋ ተደርጓል።
የሥራ ዘመናቸውን በጨረሱት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ቦታ የአዲስ ኮሚሽነር ምርጫ ማካሄድም ከዚህ ጉባኤ የሚጠበቅ ነው።
ጉባዔው በየዓመቱ የሚቀያየረው የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበርነትን በ2024 ስትመራ የነበረችው ሞሪታኒያ ስልጣኑን ለአንጎላ አስረክባለች።
የኅብረቱ ሊቀመንበር የነበሩት የሞሪታኒያው ፕሬዝዳንት ሞሃምድ ኡልድ ጋዝዋኒ ለወቅቱ የኅብረቱ ሊቀ-መንበር ሆነው ለተመረጡት የአንጎላ ፕሬዝዳንት ዧ ማኑኤል ጎሳዌስ ሎሬንሶ መልካም የሥራ ዘመን ተመኝተዋል።
አንጎላ የ2025 የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበር በመሆን ሥራዋን ጀምራለች።