ፖለቲካ
ለኢትዮጵያዊያን ቪዛ የማይጠይቁ 10 የአፍሪካ ሀገራት እነማን ናቸው?
26 የአፍሪካ ሀገራት አሁንም አፍሪካዊያንን ያለ ቪዛ ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ ከልክለዋል ተብሏል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/12/258-110223-kenya-greenlights-visits-from-all-africans-in-push-for-unhindered-continental-travel-01-scaled_700x400.jpg)
ማንኛውም የአፍሪካ ሀገራት ዜጋ ያለ ቪዛ እንዲገባ የፈቀዱ ሀገራት ቁጥር 15 ደርሷል
ለኢትዮጵያዊያን ቪዛ የማይጠይቁ 10 የአፍሪካ ሀገራት እነማን ናቸው?
የአፍሪካ ህብረት በአጀንዳ 2063 እቅዱ ላይ አፍሪካዊያን እርስ በርሳቸው ያላቸውን ንግድ እና ቱሪዝም ለማሳደግ ነጻ ቪዛ የተሰኘ ስርዓት ይፋ አድርጓል።
ህብረቱ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ይህ የአፍሪካዊያን ነጻ እንቅስቃሴ ምን ላይ እንዳለ ያስጠናውን ጥናት ይፋ አድርጓል።
በዚህ ሪፖርት መሰረትም አፍሪካዊያን በነጻ ካንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀሱ በሚል ያዘጋጀው እቅድ አጥጋቢ ለውጥ እያሳየ እንዳልሆነ አስታውቋል።
በዚህ ሪፖርት መሰረት አሁንም 26 የአፍሪካ ሀገራት ለሚመጡ አፍሪካዊያን ቪዛን ይጠይቃሉ ተብሏል።
አፍሪካዊያን ያለ ቪዛ እንዲገቡ እና እንዲወጡ የፈቀዱ ሀገራት ቁጥር 15 ብቻ ነው የተባለ ሲሆን ብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ኢ-ቪዛ ወይም የመዳረሻ ቪዛን ይፍቅዳሉ።
በዚህ መሰረትም ማንኛውም የአፍሪካ ሀገር ዜጋ ያለ ቪዛ እንዲገቡ ከፈቀዱ ሀገራት መካከል ቤኒን፣ሩዋንዳ፣ ጋና፣ ሴኔጋል፣ ኬንያ እና አልጀሪያ ዋነኞቹ ናቸው።