ለሁለት ቀናት የሚቆየው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት ባደረጉት ንግግር አዲስ የሆነ የሁለገብ ግንኙነትአማራጭ ሊኖረን ይገባል፤ በዚህ መንገድ የበለፀገች አፍሪካ መገንት እንችላን ብለዋል።
የዲሞክራሪክ ሪፐብሊክ ኮንጎ( ዲአርሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስት ከሪስቶፍ ኑቱንዱላ፤ የአፍሪከ ህብረትን የበለጠ ጠንካራ እና ውጤታማ ተቋም ለማድረግ የሪፎርም ስራዎች እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።
አፍሪካ በርካታ ፈተናዎች ተጋርጠውባታል ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ኮቪድ 19 ነው ብለዋል።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ራማፎሳ የኮቪድ 19 ለመከላከል ለሰሩት ስራ ምስጋና ይገባቸዋል፤ ያሉ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ በኮቪድ መከላከል ዙሪያ ለሰሩት ስራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ፕሬዚዳንት ራማፎሳ የኢትዮጵየ መንግስት እና ህዝብም ይህንን ጉባዔ እንዲዘጋጅ ስላደረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።
ስብሰባው በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት የስብሰባ አዳራሽ መካሄድ የጀመረ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ይካሄዳል።
በስብሰባው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማትን ጨምሮ የህብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ይሳተፋሉ።
ስብሰባው የሀገራት መሪዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማኀበረሰብ ተቋማትና በሕብረቱ ስር የሚገኙ ተቋማት የሚያደርጉት በሶስተኛው አጋማሽ ዓመት ለሚያደርጉት ጥምር ውይይት አጀንዳዎች የሚቀርቡበት ነው።