ፖለቲካ
በግድቡ ጉዳይ ላይ በአፍሪካ ህብረት በኩል የሚደረጉ የማሸማገል ጥረቶችን እንደሚደግፍ ተመድ አስታወቀ
አቶ ደመቀ ከድርጅቱ ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሐመድ ጋርም በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል
ደመቀ መኮንን ከተመድ ዋና ጸሃፊ ጋር ተወያይተዋል
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያዩ፡፡
የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት(ኦቻ) “የተዛቡ መግለጫዎች ከመስጠት እንዲቆጠብ” ኢትዮጵያ ጠየቀች
ውይይቱ በዋናነት በውስጣዊ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች በተለይም በትግራይ ጉዳይ ላይ ማተኮሩን የዋና ጸሃፊው ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በውይይቱ በድጋሚ የሰላም ጥሪን አቅርበዋል ያለው ጽህፈት ቤቱ ሰብዓዊ ተደራሽነትን ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ስለማለታቸው ገልጿል፡፡
ጉቴሬዝ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ወደ ውይይት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ድርጅታቸው በአፍሪካ ህብረት በኩል ለሚደረጉ የማሸማገል ጥረቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው ያስታወቁት፡፡
“ከሱዳን መጠለያ ጣቢያዎች የወጡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የት እንዳሉ ማረጋገጥ አልቻልኩም” - ተመድ
በአሜሪካ ኒውዮርክ በመካሄድ ላይ ባለው 76ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ በመሳተፍ ላይ ያሉት አቶ ደመቀ ከድርጅቱ ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሐመድ ጋርም በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።