የጊኒን ወታደራዊ እርምጃ የመራዉ የፈረንሳይ ጦር አባል የነበረ ነዉ
የአፍሪካ ህብረት ጊኒን ከአባልነት አገደ።
የአፍሪካ ህብረት ጊኒን ከአባልነት ያገደው ፕረዝዳንት አልፋኮንዴ በወታደራዊ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ ነው።
ህብረቱ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው፣ የምእራብ አፍሪካ ሀገራት የንግድ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ጊኒን ከአባልነት ካገደ ከአንድ ቀን በኋላ ነዉ።
ሀገራቱ እግድ ከመጣል በተጨማሪ በጊኒ ህገመንግስታዊ ስርአት እንዲሰፍን ጠይቀዋል።
የጊኒ ልዩ ኃይል ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ይገኛል።
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ በጊኒ የተወሰደው ወታደራዊ እርምጃ ተወግዟል።
በጊኒ የተካሄደውን ወታደራዊ እርምጃ የመራው የፈረንሳይ ጦር አባል የነበረው ኮሎኔል ማማዱ ዱምቢያ መሆኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል።