ልዩልዩ
የሚወደውን ድምጻዊ ለመምሰል 40 ጊዜ ቀዶ ጥገና ያደረገው ወጣት
አርጀንቲናዊው ፍራን ማሪያኖ ድምጻዊ ማርቲንን ለመምሰል 40 ጊዜ የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና አድርጓል
የፖፕ ስታሩ ሪኪ ማርቲን ከዓለማችን 100 መልከ መልካም ሰዎች መካከል አንድኛው ነው ተብሏል
ሪኪ ማርቲን በዓለማችን ካሉ ተወዳጅ ድምጻዊያን መካከል አንዱ ሲሆን በተለይም በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ አህጉራት ተወዳጅ ነው፡፡
አርጀንቲናዊው ፋን ማሪኖ ደግሞ የዚህ ድምጻዊ አድናቂ ነው የተባለ ሲሆን እሱን ለመምሰል ባደረጋቸው የቀዶ ጥገና ህክምናዎች ምክንያት የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡
ማሪኖ በተፈጥሮ የተሰጡ የሰውነት ክፍሎቹን በቀዶ ትገና በማስወገድ ሪኪ ማርቲንን ለመምሰል ላለፉት ዓመታት ሲለፋ መቆየቱን ገልጿል፡፡
- ፊቷን ለማሳመር 100 ሺህ ዶላር ለፕላስቲክ ቀዶ ህክምና ያወጣችው ጃፓናዊት
- ፈተና ለመኮረጅ ጆሮው ውስጥ የብሉቱዝ ማዳመጫ በቀዶ ጥገና ያስተከለው ህንዳዊ ተማሪ ተያዘ
እስካሁን የአይን፣ አፍንጫ፣ አገጭ እና ሌሎችንም የሰውነት ክፍሎቹን ያስወገደ ሲሆን ይህ ሁሉ ጥረቱ ደግሞ ድምጻዊ ማርቲንን ለመምሰል ነው፡፡
የምወደውን ድምጻዊ ለመምሰል ራሴን መስዋዕት አድርጌያለው ያለው ይህ አርጀንቲናዊ ያደረጋቸው ቀዶ ጥገናዎች ህይወቱን እስከማሳጣት የሚደርሱ ናቸውም ተብሏል፡፡
ግለሰቡ ይህን በማድረጉም ለብዙ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳቶች መዳረጉንም አስታውቋል፡፡
እኔ ያደረኩት ያልተገባ ድርጊት እንደሆነ አውቃለሁ፣ ሌሎች ወጣቶች ከእኔ ህይወት ሊማሩ ይገባል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል ሲል ለየት ያሉ ዘገባዎችን በማስነበብ የሚታወቀው ኦዲቲ ሴንትራል ገልጿል፡፡