ቦሪስ በ2020 ከኮቪድ ህመም ጋር ተያያዞ የሳይነስ ኢንፌክሽን እንደነበራቸው ነው ተገልጿል
ቀላል “የአፍንጫ ቀላል ቀዶ ጥገና” ያደረጉት የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በማገገም ላይ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት (ዳውኒንግ ስትሪት) የቀዶ ጥገና ሂደቱ የተሳካ እንደነበር ያስታወቀ ሲሆን ቦሪስ አሁን ላይ አስፈላጊውን እረፍት በመውሰድ ላይ ናቸው ብሏል፡፡
የጆንሰን ቃል አቀባይ ማክስ ብሌን ፤ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ አሁን ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል ብለዋል፡፡
ቀዶ ጥገናው አስቀድሞ ታቅዶ የነበረና በለንደን ሆስፒታል በመንግስት የገንዘብ ድጋፍ ለብሔራዊ ጤና አገልግሎት በሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች የተደረገ መሆኑም ተናግረዋል ቃል አቀባዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማክሰኞ ወደ ስራ ከመመለሳቸው በፊት መደረግ ያለባቸውን ማንኛውንም ለጤናቸው “ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎች” ሊወስኑ ይችላሉ ያሉት ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብናቸው፡፡
ቦሪስ በ2020 ከኮቪድ ህመም ጋር ተያያዞ የሳይነስ ኢንፌክሽን እንዳለባቸው ሳይረዱ ቆይተው ለዚህ መዳረገቻውም ነው የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፡፡
ራብ፤ ጠቅላይ ሚኒሰትር ቦሪስ ጆንሰን በወረርሺኙ ኩፉኛ ተጎድተው ወደ ከፍተኛ እንክብካቤ በገቡበት ወቅት የእሳቸውን ቦታ ተክተው ኃላፊነታቸው የተወጡ ብቁ መሪ እንደነበሩ የሚታወስ ነው፡፡
ራብ በኋላ ላይ “ጆንሰን ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ፍራቻ እንዳላቸው ለኮንሰርቫቲቭስ ፓርቲ በቪዲዮ ኮንፈረንስ” የተናገሩበት አጋጠሚም አይዘነጋም ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ ቦሪስ ጆንሰን አሁን ከገጠማቸው የጤና እክል ጋር ተያይዞ በዚህ ሳምንት በሩዋንዳ ይካሄዳል ተብሎ ወደ ሚጠበቀው የኮመንዌልዝ የመሪዎች ስብሰባ ካልተጓዙ ፤ እሳቸው ተክተው ይጓዛሉ ተብሎም ይጠበቃል።