ፕሬዝዳንት ዩን ለጉዳቱ የተሳሳቱ የአደጋ ምላሾችን ተጠያቂ አድርገዋል
የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል ለቀናት በዘለቀው ከባድ ዝናብ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 40 በማሻቀቡን አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ ባለስልጣናት የአደጋ ምላሽ ህጎችን አለተከተሉም በማለት ተጠያቂ አድርገዋል።
በሰኔ ወር መጨረሻ የጀመረው የዝናብ ወቅት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ከሀሙስ ጀምሮ ጎርፍ በማዕከላዊ እና ደቡብ ክልሎች ጉዳት አድርሷል።
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር በሀገሪቱ ውስጥ ዘጠኝ ሰዎች ጠፍተዋል እና 34 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ብሏል።
ክስተቱ ደቡብ ኮሪያ የጎርፍ ጉዳትን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት በምታደርገው ጥረት ላይ ጥያቄዎችን አስነስቷል።
የአደጋ ምላሽ ስብሰባ የጠሩት ፕሬዝዳንት ዮን፤ በተጋላጭ አካባቢዎች የአስተዳደር ጉድለት ምክንያት ሁኔታው የከፋ መሆኑን አምነዋል።
ወደ 900 የሚጠጉ የእሳት ቃጠሎ፣ፖሊስ እና ወታደራዊ ኃይል በጀልባዎች፣ በድሮኖች እና ሌሎች መሳሪያዎችን በመጠቀም የነፍስ አድን ስራ ላይ ተሳትፈዋል ተብሏል።