በፓኪስታን በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1ሺ 500 ደረሰ
ጎርፉ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ጉዳት ደርሷል
የጎርፍ ውሃ ወደ ኃይል ማመንጫ ጨምሮ ቁልፍ ወደሚባሉ ቦታዎች እንዳይወጣ ባለስልጣናቱ መከላከያ እያሰሩ ነው
በፓኪስታን ያልተጠበቀ ጎርፍ ሰፊ ቦታን በማጥለቅለቁ ምክንያት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር እካን 1ሺ 500 መድረሱን ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
ሀገሪቱ በጎርፉ ጉዳት የደረሰባቸውን ሚሊዮኖች ለመርዳት ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ ሮይርስ ዘግቧል፡፡
በከፍተኛ የሞንሱን ዝናብ እና በበረዶ መቅለጥ የተከሰተው ካባድ ጎርፍ ፓኪስታን ሰፊ ቦታ በመሸፈን ከሀገሪቱ ጠቅላላ 220 ሚሊዮን ህዝብ በ33 ሚሊዮን ሰዎች ላይ ጉዳት አስከትሏል፡፡ በአደጋው ቤቶች ተወስደዋል፤የትራንስፖርት መሰረት ልማት ፈርሷል፤ እህል እና የቤት እንስሳት የተሰወዱ ሲሆን በአጠቃላይ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ጉዳት ደርሷል፡፡
በጎርፍ አደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1ሺ 486 ሲሆን ከእነዚህም መካከል 530 የሚጠጉ ህጻናት መሆናቸውን የብሄራዊ የአደጋ መከላከል ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የጎርፍ ውሃ ወደ ኃይል ማመንጫ ጨምሮ ቁልፍ ወደሚባሉ ቦታዎች እንዳይወጣ ባለስልጣናቱ መከላከያ እያሰሩ ነው፡፡