ሱዳን በጎርፍ አደጋ ሳቢያ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱበትን ጊዜ አራዘመች
ከ100 በላይ ሰዎች በሱዳን የጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል
በሱዳን በጎርፍ አደጋ ከ600 በላይ ትምህርት ቤቶች ተጎድተዋል
ሱዳን በበርክታ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እያጋጠመ ባለው የጎርፍ አደጋ ሳቢያ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱበት ጊዜን አራዘመቸ።
ጎረቤት ሀገር ሱዳን በከባድ ዝናብና ጎርፍ መቸገሯ ተገልጿል።
ካሳለፍነው ሰኔ ወር ጀምሮ ባሉት ሶስት ወራት ውስጥ በጎርፍ የተወሰዱ ዜጎች ቁጥር 100 ገደማ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።
ከዚህ በተጨማሪም ጎርፉ ከግለሰቦች በተጨማሪ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት መሰረተ ልማቶች የግለሰቦች ኢንቨስትመንት ስራዎች መውደማቸው ተነግሯል።
ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ ትምህርት ቤቶች አንዱ ሲሆኑ በጎርፍ አደጋው 623 ትምህርት ቤቶች ተጎድተዋል።
ይህንን ትትሎም ሱዳን የፊታችን መስከረም 22 ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ትንርት ቤቶችን የመክፈት መርሃ ግብር መራዘሙን የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የትምህርት ማስጀመሪያ ጊዜው የተራዘመው ትምህርት ቤቶቹ ከደረሰባቸው ጉዳት አንጻር መልሶ ግንባታ ስለሚያሰፈልጋቸው ነው ተብሏል።
በሱዳን በየዓመቱ የጎረፍ አደጋ የተለመደ ሲሆን ዜጎችን ከመግደሉ ባለፈ ለንብረት ውድመት እንደሚዳርግ የተገለጸ ሲሆን የዘንድሮው የጎረፍ አደጋ አስከ ቀጣዩ ጠቅምት ድረስ ሊዘልቅ ይችላል ተብሏል።
እስካሁን ባለው የክረምት ወቅት በደቡባዊ ሱዳን ክፍል 50 መንደሮች ክፉኛ በጎርፍ ተጠቅተው ከ65 ሺህ በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን የተመድ ሪፖርት ያስረዳል።
ባሳለፍነው ዓመት በተመሳሳይ የክረምት ወራት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ሱዳን የሶስት ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንድታውጅ ያስገደዳት ሲሆን ከ110 ሺህ በላይ ቤቶች በጎርፍ ወድመው ከ650 ሺህ በላይ ዜጎች መጎዳታቸው ይታወሳል።