40ኛው የገልፍ ትብብር ምክር ቤት ጉባኤ በሳዑዲ አረቢያ መካሄድ ጀምረ
በገልፍ የአረብ ሀገራት መካከል መተባበርን ለማጠናከርና በሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚመክረዉ 40ኛው የትብብር ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ በሳዑዲ ዋና ከተማ ሪያድ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የኦማንን ቦታ በመተካት የወቅቱን ስብሰባ እየመራች ትገኛለች፡፡
ጉባኤው በገልፍ ባህረ ሰላጤ ሀገራት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ዙሪያ ውይይት የሚያደርግ ሲሆን በተለይ በደህንነት እና የመከላከያ ትብብር ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡
ይህ መደበኛ ጉባኤ የገልፍ አረብ ሀገራት ትብብር ምክር ቤት እንደአውሮፓውያኑ በ1981 ከተመሰረተ ጀምሮ 40ኛዉ ጉባኤ ሲሆን ከጉባኤዎቹ ዉስጥ የወቅቱን ጉባኤ ጨምሮ 9ኙ በሳዑዲ አረቢያ እንዲሁም 7ቱ በኩየት ተካሂደዋል፡፡
ሌሎቹ ጉባኤዎች ደግሞ በባህሬን፣በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ፣ በኳታርና በኦማን ተካሂደዋል፡፡