ኢትዮጵያ በተወሰኑ አትሌቶች አማካኝነት ከአበረታች መድኃኒት ጋር ስሟ እየተነሳ ነዉ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ እንደተናገሩት አበረታች መድኃኒት የመጠቀም ፍላጎት እንደ ሀገር በጥብቅ የተወገዘ ቢሆንም ሀገሪቱ በተወሰኑ ሯጮች አማካኝነት እዚህ ችግር ዉስጥ ገብታለች ብለዋል፡፡
የአበረታች መድኃኒት ጉዳይ “ሀገራችንን ጨምሮ ዓለምን እያስጨነቀ ያለ ጉዳይ ነዉ” ያሉት ሻለቃ ደራርቱ አበረታች መድኃኒት የመጠቀም ችግር እንዲቀረፍ ከቤተሰብ ጀምሮ ጎጅነቱን የሚያሳይ ግንዛቤ መፈጠር እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
እስካሁን በአለም አቀፍ ደራጃ 2500 የሚሆኑ ምርመራዎች የተደረጉ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ 9 የሚሆኑት የኢትዮጵያ አትሌቶች አበረታች መድኃኒት መጠቀማቸዉ እንተረጋገጠ የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጸረ አበረታች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ናቸዉ፡፡
አበረታች መድኃኒት ተጠቅመዉ የተገኙት የኢትዮጵያ አትሌቶችና አበረታች መድኃኒቱን ሲሸጡ የነበሩት መድኃኒት ቤቶች እርምጃ እነደተወሰደባቸዉ አቶ መኮንን ተናግረዋል፡፡
የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ምክትል ኃላፊ ቶማስ ካፕዴቪሌ በበኩላቸዉ ማናጀሮችና አሰልጣኞች፣ አትሌቶች አበረታች መድኃኒትን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ ሊመክሯቸዉ ይገባል ብላዋል፡፡
ተጋላጭነትን ዜሮ ማድረግ ባይቻልም አትሌቶችን በማስተማር የአበረታች መድኃኒት ተጋላጭነትን መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡